የኢንስቲትዩቱ የመስቀል ፍላወር ቅርንጫፍ

የኢንስቲትዩቱ የአያት ጨፌ ቅርንጫፍ

Raeesh
የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት

የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከዚህ ቀደም ተበታትነው ሲሰሩ የነበሩ የሕግ ጥናትና ምርምር፣ የፍትሕ አካላት ባለሙያዎች ሥልጠና፣ የፍትሕ ሥርዓት እና የሕግ ትምህርት ማሻሻያ ሥራዎችን በማካተት በአንድ ተቋም እንዲልጠቃለል የተደረገ ተቋም ሲሆን ይህም ተግባራት በአግባቡ እንዲከናወኑ በማድረግ፣ የኃላፊነት ድግግሞሽን በማስቀረትና ውጤታማ ሥራዎችን ለማከናወን እንደሚረዳ በመገንዘብ የተቋቋመ ነው፡፡
ይህ በአዲስ የተዋቀረው ኢንስቲትዩቱ በ2010 ዓ.ም የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት በመባል በአዋጅ ቁጥር 1071/2010 ዓ.ም እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በአዲስ መልክ መዋቀሩን ተከትሎ የተቋቋመበትን ዓላማ ለመፈጸም የሚያስችለውን አደረጃጀት በጥቅምት 2010 ዓ.ም እንዲሁም ከበላይ አካላት በተሰጡ የማሻሻያ ሀሳቦች መነሻነት ለሁለተኛ ጊዜ በታኅሣሥ 2012 ዓ.ም አዘጋጅቶ አስጸድቋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በ2014 ዓ.ም በተደረገው የተቋማት ሽግሽግና አደረጃጀት መሰረት የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ከሚለው መጠሪያ ስያሜ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የሚል መጠሪያ እንዲገያኝ እና አዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀት እንዲያዘጋጅ ተደርጓል፡፡