የዋና ዳይሬክተር ስልጣንና ተግባር
የፌዴራል የፍትህና ሕግ ኢንስቲቲዉት በሚንስቴር ማዕረግ በዋና ዳይሬክተር ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የሚመሩት ክቡር የአምባሳደር ደግፌ ቡላ ሲሆኑ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የኢንስቲትዩቱን ሥራዎች ይመራል፣ ያስተዳድራል፡፡ የዋና ዳይሬክተሩ ተጠሪነት ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ሆኖ የሚከተሉት ተግባራት ይኖሩታል፡፡ የኢንስቲትዩቱን ሥልጣንና ተግባር በሥራ እንዲውል ያደርጋል፤ የኢንስቲትዩቱን ዓላማ የሚያስፈጽሙ ባለሙያዎችን መንግስት በሚያወጣው መመሪያ መሰረት እንዲሁም ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞችን በፌደራል ፐብሊክ ሰርቪስ ሕግ መሰረት ይቀጥራል፤ ያስተዳድራል፤ ያሰናብታል፤ የኢንስቲትዩቱን ኘሮግራሞችና በጀት አዘጋጅቶ ለመንግስት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል፤ የኢንስቲትዩቱን ሥልጣን እና ተግባራት ሥራ ላይ ለማዋል ዕቅድ፣ መርሃ-ግብር እና በጀት አዘጋጅቶ ለበላይ አካል ያቀርባል፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል፤ ለኢንስቲትዩቱ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ኘሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል፤ያስተዳድራል፣
የኢንስቲትዩቱን የሥራ አፈጻጸም እና የሂሳብ ሪፖርት ያቀርባል፤ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ኢንስቲትዩቱን ይወክላል፤ ዋና ዳይሬክተሩ ለኢንስቲትዩቱ ሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ከሥልጣን እና ተግባራቱ በከፊል ለምክትል ዋና ዳይሬክተሮች እና ለሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል፣
የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት
አቶ አበበ ሹመት የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ሃላፊ
የተቋማችን ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ተጠሪ የሆኑ ስራ አስፈጻሚ ክፍሎች የኦዲት ሥራ አስፈጻሚ ፤ የህዝብ ግኑኝነት እና የኮምንኬሽን ስራዎች ፤
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ እንዲሁም የፀረ ሙስና እና የስነምግባር የመከታተል ስራዎችን የሚሰራ ነዉ፡፡ ጽ/ቤቱ በተቋሙ የ10 ዓመት እስትራቴጂክ
ፕላን ላይ በመመርኮዝ ለጽ/ቤቱ ተጠሪ የሆኑትን ስራ አስፈጻሚ ክፍሎች በማስተባበር የአመታዊ እቅድን በአግባቡ መዘጋታቸዉና ተፈጻሚነታቸዉን
ወቅታዊ ክትትል በማድረግ ስራዉን እየተገበር ይገኛል፡፡
በተጨማሪም ለጽ/ቤቱ ተጠሪ የሆኑ እያንዳንዱን የስራ አስፈጻሚ ላይ ትኩረት በማድረግ ከዉስጥ ኦዲት ስራዎችን ፤ ከፀረ ሙስና እና ስነ ምግባር
ክትትልና እርምጃዎች በተጨማሪም በሴቶችና ማህበራዊ አካቶ ትግበራ ስራዎችን በኮምንኬሽን እና ህዝብ ግኑኝነት ተግባራት ጋር በማረቅ የሚሰራ ነዉ፡፡
ከተቋማችን አጋር ጀስቲስ ፎር ኦል ያዘጋጀዉ ሀገር አቀፍ የፍትህ አካላት የጋራ የምክክር መድረክ ላይ
የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት በዋናነኝነት ከሚሰራቸዉ ስራዎች መሀከል፡-
- በተቋሙ የፋይናንሻል፣ የክዋኔ እና ፐርፎርማንስ ኦዲት እንዲከናወኑ ያደርጋል፣ የኦዲት ግኝቶች መሰረት በማድረግ የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡
- የተቋሙ ሂሳብ በውጭ ኦዲት እንዲመረመር ያደርጋል፣ በተሰጡ ግኝቶች ላይ የማስተካከያ እርምት እርምጃዎች እንዲወሰድ ያደርጋል፣ መወሰዱን ያረጋግጣል፡፡
- የተቋሙ የኦዲት ሥራዎች የኦዲት ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፡፡
- ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ እንቅስቃሴዎችን በመከታተል በመስሪያ ቤቱ ተግባራት ላይ የሚኖራቸውን እንደምታ ለሥራ አመራሩ ያሳውቃል፡፡
- የተዘጋጁ የተለያዩ የመግባቢያ ስምምነት /memorandum of understanding/ ሰነዶችን ያረጋግጣል፣ ይወስናል፣ ለበላይ አካል መቅረብ ያለባቸውን ለውሳኔ ያቀርባል፣ ይከታተላል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ከሌላ ወገን ጋር የሚያደርጋቸው ድርድሮችና ስምምነቶች የሀርን ብሎም የተቋሙን ጥቅም የሚያስጠብቁ እና ውጤታማ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣
ለጽ/ቤቱ ተጠሪ የሆኑ የስራ ክፍሎች


በአጠቃላይ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት የጽ/ቤቱን ሥራዎች በመምራት፣ ውሳኔ የተሰጣቸውን ጉዳዮች አፈጻጸም በመከታተል፣ የተቋሙ አደረጃጀቶች እንዲጠናከሩ ድጋፍ በማድረግ፣ የአሠራር ሥርዓት በመቀየስና አፈፃፀማቸውን በመገምገም የተቋሙን ግቦች እንዲሳኩ የማድረግ ተግባራትን ያከናዉናል ። ለጽ/ቤቱ ተጠሪ የሆኑ የስራ ክፍሎች፡-
ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በ2016 የፍትህ አካላት የጋራ የምክክር መድረክ ላይ
የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ከማንኛዉ የፍትህ አካላት፤ መንግስታዊ ተቋማት እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ በፍትህና ሕግ ዘርፍ፤ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ እና በስነምግባርና ፀረ ሙስና አብሮ እየሰራ ሲሆን ወደፊትም ይህንን ትኩረት በማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ለበለጠ መረጃ ያግኙን፡፡
አቶ አበበ ሹመት፡- የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ሀላፊ
ስልክ፡-
ሞባይል፡-0913923383 / 0943164696
ኢሜል፡-hiyenteabebe@gmail.com
የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ስራዎች በጥቂቱ
የፌደራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት አመራሮች ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ነሃሴ 2016 ዓ.ም
እንኳን አደረሳችሁ!
በዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት የተዘጋጀ የተቋሙ አዲስ መዋቅር አስመልክቶ የተደረገ ስብሰባ መስከረም 2016 ዓ.ም
አጋር ተቋማት
የተቋማችን አጋር አዉሮፓን የህብረት
European Union
የተቋማችን አጋር ጀስቲስ ፎር ኦል
Justice for All PF Ethiopia
Our Partner
በ2015 ዓ.ም በጽ/ቤቱ የተዘጋጀ የአረንጓዴ አሻራ
የፌዴራል ፀረ ሙስና ምክትል ኮምሽነር እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት
20ኛዉ ሀገር - አቀፍ የፀረ - ሙስና ቀን በአል በፍርድ ቤት ዘርፍ
በሙስና የጋራ ጠላታችን ነዉ! በህብረት እንታገል! በሚል መሪቃል ሲከበር ህዳር 2016 ዓ.ም