የተከበሩ አቶ ምትኩ ማዳ፡- ምክትል ዋና ዳይሬክተር:- የፍትህና ሕግ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

የጥናት አዉደ ዕራይ በ2015 ዓ.ም

የጥናት አዉደ ዕራይ በ2015 ዓ.ም

የጥናት አዉደ ዕራይ በ2015 ዓ.ም

Raeesh
የተከበሩ አቶ ምትኩ ማዳ

የፌደራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይ/ር (ሚኒስቴር ዴኤታ)
የፍትህና ሕግ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

የፌደራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት በአዋጅ ቁጥር 1071/2018 መሠረት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስትን በተሟላ ሁኔታ ስራ ላይ ለማዋል፣ መልካም አስተዳደርን እና ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን እውን ለማድረግ የሚረዱ የፍትህና የሕግ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ አንዱና ተቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡
ኢንስቲትዩቱም ይህን ተልዕኮውን ለመወጣት ያስችለው ዘንድ በምክትል ዋና ዳይሬክተር የሚመራ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ያደራጀ ሲሆን በስሩም የፐብሊክ ህጎች ጥናትና ምርምር ስራ አስፈፃሚ፣ የሲቪል ህጎች ጥናትና ምርምር ሥራ አስፈፃሚ እና የፍትህ ስርዓት ጥናትና ምርምር ሥራ አስፈፃሚ ይገኛሉ፡፡ ተቋሙም እንደ ጥናቱ ልዩ ባህሪ ስራዎችን ለማከናወን በኢንስቲትቱ በተለያየ ደረጃ ከሚገኙ የሕግ ተመራማሪዎች በተጨማሪ ከሌሎች ባለድርሻ ተቋማት እና ምሁራን ጋር በመቀናጀት ጥናቶችን እያከናወነ ይገኛል ፡፡
በተያዘው የበጀት አመትም ከተለያዩ የተቋሙ ባለድረሻ አካላት ጥናት እንዲሰራባቸው የቀረቡትን ጨምሮ ኢንስቲትዩቱ ሊሰሩ ይገባቸዋል የሚላቸውን ርዕስ ጉዳዮችን ለይቶ በማጽደቅ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ የጥናትና ምርምር ዘርፉ ርዕሰ ጉዳዮቹ ሊጠኑ የሚችሉና ከተቋሙ ተልዕኮ ጋር ያላቸው ቀጥተኛ ግንኙነት( Relevance and Researchable ),ወቅታዊነት (Timiliness), ጠቃሚ እና ችግር ፈቺነት (Significant And Empirical effect) እንዲሁም በተነጻጻሪነት በሁሉም የሕግ አስከባሪና ዳኝነት አካላት ላይ ተጽዕና ማድረስ የሚችሉ ( Cross Cutting Effects) መሆናቸውን ከግምት በማስገባት ስድስት የጥናት ርዕሰ ጉዳዮች መርጦ የጥናት መነሻ ሃሳቦች ላይ ውይይቶችን ካደረገ በኋላ ለአማካሪ ምክር ቤት ያቀርባል፡፡
በዋና ዋና መመዘኛዎች መሰረት በዘርፉ እንዲጠኑ የተመረጡ ጥናቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

  1. “የአሰተዳደር ወሰን የሕግ ማዕቀፍ በኢትዮጵያ፡ ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎች ” ፣
  2. “የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአሰተዳደር ሥልጣን ተዋረድ እና ግንኙነት” ፤
  3. “የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ደረጃና እርከን ያለወጣላቸው የወንጀል ድንጋጌዎች አፈጻጸም ” ፤
  4. “ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጎጂዎች የሚካሱበት የሕግ ማዕቀፍ እና አሰራር ስርዓት” እና
  5. “የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ሥነ-ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አተገባበርና አፈጻጸም ” ናቸው፡፡

እነዚህም የጥናት ርዕሰ ጉዳዮች በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲሰሩ በማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፡፡