(መጋቢት 15/2017) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ዓቃቢያነ ሕግ የሚሰጠው አምስተኛ እና የመጨረሻ ዙር ስልጠና ዛሬ በአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ አዳራሽ ተጀመሯል፡፡ በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ተክሌ በዛብህ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በእንደዚህ አይት ስልጠናዎች የሚያደርገውን ቀና ትብብር በማመስገን ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን ስልጠናው ከመሰጠቱ በፊት ጥናት ተሰርቶ የአቃቢ ህጎችን ፍላጎት በመጭመቅ የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ በኮሊደር እና በሌሎች ልማቶች ላይ ፈጣን ግስጋሴ እያሳየች ያለች ከተማ ነች ያሉት ኃላፊው እነዚህ ሥራዎችን ለማሳለጥ የህግ ባለሙያዎች፣ ከተማ አስተዳደሩ በሚፈልገው ፍጥነት ልክ መሮጥና የሚጋጥሙ ችግሮችን መፍታት ስለሚገባቸው የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የስልጠናውን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት በሚንስቴር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው ይህ ሥልጠና በዘርፉ በቂ ዕውቀትና ግንዛቤ ያላቸውን አሰልጣኞች በመጠቀም እየተሰጠ ያለ ሥልጠና እንደሆነ በመጥቀስ ኢንስቲትዩቱ በበጀት ዓመቱ ሊሰራቸው ካቀዳቸው ሥራዎች መካከል ቅድሚ በመስጠት የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ ሥልጠና በኋላ የፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ሥልጠናው ያመጣው ለውጥ ምንድን ነው የሚለውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ጥናት ያካሂዳከል ያሉት ሚንስቴር ዴዔታው በመሆኑም ይህን ሥልጠና በአግባቡ በመከታተል በእያንዳንዱ ክፍለ ከተማ ስትመለሱ ተጋባራዊ ማድረግና ያልሰለጠኑ ባልደረቦቻቹህን ማብቃት ይጠበቅባቹኋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በማስተዋወቅ ንግግራቸውን የቀጠሉት የተከበሩ አቶ ዘካርያስ በዚህም ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ፣ ለፍትሕ ዘርፉ የአቅም ግንባታ ሥልጠና መስጠት፣ የፍትሕ እና ሕግ ማሻሻያዎች እርስ በርዕስ እንዲደጋገፉ ማድረግና የአገሪቱ የፍትሕና ሕግ መረጃ ማዕከል ሆኖ እያገለገለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ይህ ሥልጠና አምስተኛና የመጨረሻው ዙር ሲሆን በአጠቃላይ ከ200 በላይ ዓቃቤ ሕጎች ሥልጠናውን እንዲወስዱ ተደርገዋል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(መጋቢት 12/2017 ዓ.ም) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በፍርድ ቤት መር አስማሚነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ዛሬ በአዲስ አበባ እየሰጠ ነው፡፡ በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዳኛ አበበ ሰለሞን በንግግራቸው ከአሁን በፊት አማራጭ የሙግት መፍቻ የሚል ስያሜ እንደነበረውና ይህ ደግሞ ሌላ የተሻለ ነገር ከጀርባው እንዳለ የሚሳይ እንደነበረ በመጥቀስ፤ በአሁኑ ሰዓት ይህ ፍርድ ቤት መር አስማሚነት የፍትሕ ስርዓት ተመራጭ የሙግት መፍቻ መንገድ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ ተከራካሪ ወገኖች በመደበኛ የዳኝነት ሥርዓት ችግሮቻቸውን ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ በፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሥርዓትን መጠቀም ይበጃል ያሉት የጽህፈት ቤት ሃላፊው በዚህም አሸናፊና ተሸናፊ ወገን ሳይኖር ሁለቱንም ተከራካሪዎች ጤናማ ግንኙነታቸውን በማስጠበቅ፣ የይቅር ባይነትን ስሜት በማዳበር እና የማህበረሰባዊ ዕሴቶችን ባስጠበቀ መልኩ ችግሮቻቸውን መፍታት ይችላሉ ብለዋል፡፡ ይህ ሥልጠና ከፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባር ሲዘጋጅ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ያሉት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሪት ሉሊት አድነው የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ረዳት ዳኞች፣ የአስማሚነት ዕውቀትና ክህሎታቸውን እንዲያጎለብቱ በማሰብ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል በፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የዳኝነት ሥልጠና ማስተባበሪ ዴስክ ኃላፊ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ታለ በንግግራቸው ሥለ ኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ ስራዎች ንግግር በማድረግ የጀመሩ ሲሆን በዚህም ለፍትህ ዘርፉ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ማድረግ፣ የሃገሪቱ የሕግና ፍትሕ መረጃ ማዕከል ሆኖ ማገልገልና የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያዎችን መደገፍ ተቀዳሚ ስራዎቻችን ናቸው ያሉ ሲሆን ይህ ስልጠናም የስራችን አንድ አካል ነው ብለዋል፡፡ ስልጠናው ብዙ በጀት ፈሰስ እንደተደረገበት የተናገሩት አቶ ቴዎድሮስ በመሆኑም ሰልጣኞች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ልምድ መቅሰምና ያለንን በማከፈል የሰለጠናቸውን ስልጠናዎች ተግባር ላይ ማዋል ይገባናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ስልጠናው ከፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15 ረዳት ዳኞች፣ ከመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ደግሞ 35 ረዳት ዳኞች የሚሳተፉበት ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(መጋቢት 1/2017 ዓ.ም) የአማራ ክልል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ቦርድ አባላት ዛሬ በፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት አያት ጨፌ ቅጥር ግቢ በመገኘት የስራ ጉብኝት አደርገዋል፡፡ የክልሉ የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የፌዴራሉ ቅጂ መሆን አለበት ያሉት የቦርዱ አባላት በመሆኑም የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የተዋቀረበት መዋቅርና መሰል የስራ መመሪዎችን በሚመለከት መረጃ ተለዋውጠዋል፡፡ በኢንስቲትዩቱ አዳዲስ የሚስተካከሉና እየተስተካከሉ ያሉ የስራ መመሪያዎችን፣ የኢ-ለርኒንግ ስርዓት፣ የሚቋቋመው ቦርድ ተግባርና ሃላፊነት እንዲሁም ከፍተኛ ሃላፊዎችን በሚመለከት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ መረጃ የሰጡ ሲሆን የተቋሙን ተግባር፣ ሃላፊነት፣ መዋቅር፣ አደረጃጀት፣ የሰው ሃይልና የስራ ደረጃን በሚመለከት ደግሞ የኢንስቲትዩቱ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ምትኩ ማዳ ለቦርድ አባላት ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የቦርድ አባላቱ የኢንስቲትዩቱን የተለያዩ የማሰልጠኛ ክፍሎች በመዘዋወር የጎበኙ ሲሆን የአሰራርና የመዋቅር ሁነቶችን በዚህ መልኩ በማግኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የአማራ ክልል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የቦርድ አባላት ቀድመው መዋቀራቸው እንደመልካም አጋጣሚ የተነገረ ሲሆን በፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ያገኙትን መረጃና አሰራር ተግባራዊ ለማድረግም አያስቸግርም ተብሏል፡፡ በዕለቱ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ የአማራ ክልል የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት እና የኢንስቲትዩቱ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አለም አንተ አግደው፣ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና ሌሎች የቦርዱ አባላት በቦታው በመገኘት ጉብኝቱን አካሂደዋል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(የካቲት 25/2017 ዓ.ም) በፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት፣ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ቋንቋዎች አካዳሚና በጀስቲስ ፎር ኦል በጋራ ትብብር እየተዘጋጀ የሚገኘውን የኦሮምኛ ቋንቋ የሕግ መዝገበ ቃላት የአንድ ዓመት አሰራር ቆይታ እና የሚገኝበት ደረጃ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ግቢ እየተገመገመ ይገኛል፡፡ በዕለቱ የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የቋንቋዎች አካዳሚ ዲን ዶ/ር ዮሃንስ ሃድጎ በንግግራቸው የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት በሕግ መዝገበ ቃላቶች ላይ እየሰራ ያለውን በጎ ተግባር ያመሰገኑ ሲሆን ከአፋን ኦሮሞ የሕግ መዝገበ ቃላት መጠናቀቅ በኋላ በሌሎች ቋንቋዎችም አብረን መስራት እንችላለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ለግምገማ የበቃው የኦሮምኛ ቋንቋ ሕግ መዝገበ ቃላት የደረሰበትን ደረጃ፣ ሁሉንም የአፋን ኦሮሞ ተናጋሪዎች ዘዬ የዳሰሰ መሆኑንና የተሻለ ተደራሽ ለማድረግ ምን ማድረግ እንዳለብን የምንገመግምበት ዕለት ነው ያሉት ዶ/ር ዮሃንስ አክለውም ከተሳታፊዎች ገንቢ ሃሳቦችን እንጠብቃለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላፈዋል፡፡ በሚንስትር ማዕረግ የፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በመክፈቻ ንግግራቸው ፍትህ እዲሰፍን፣ ሰላም እንዲመጣና ሁሉም የሚተሳሰብባትን አገር ከመገንባት ረገድ ከሳሽ፣ ተከሳሽ፣ ዓቃቢያነ - ሕግ፣ ዳኞችና ፖሊሶች የሚግባቡበት አንድ ወጥ የሆነ የህግ ቋንቋና ፍቺ ያስፈልጋል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉ ሲሆን ለዚህ ደግሞ በአገርኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የሕግ መዝገበ ቃላቶችን ማበልጸግና ማሳተም አይነተኛ መፍትሔ ነው ብለዋል፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግ በተለያዩ የአገር ውስጥ ቋንቋዎች የህግ መዝገበ ቃላቶችን እያዘጋጀን እንገኛለን ያሉት አምባሳደሩ የዛሬው ፕሮግራምም የኦሮምኛ ቋንቋ ሕግ መዝገበ ቃላት እስካሁን የደረሰበትን ደረጃ እና የአቀራረብ ዘዬ ለመገምገም የታለመ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በአሁን በፊት የአማርኛ ቋንቋ ሕግ መዝገበ ቃላት ታትሞ ለንባብ መብቃቱን የተናገሩት ሚንስቴሩ የኦሮምኛ ቋንቋ ሕግ መዝገበ ቃላት ሕትመት ከተጠናቀቀ በኋላም በሌሎች የአገር ውስጥ ቋንቋዎች እንደሚቀጥል ተናግዋል፡፡ የአፋን ኦሮሞ የሕግ መዝገበ ቃላት ህትመት በመጽሃፍ ብቻ ሳይሆን በሞባይል መተግበሪያ መልኩም እየበለጸገ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ጥሪ የተደረገላቸው እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሕግ ዘርፉ ከፍተኛ አመራሮችና ሙህራንና ተገኝተው ሃሳብ አስተያዬት እየሰጡበት ይገኛል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(የካቲት 19/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በመንግስት አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በአዲስ አበባ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለሰራተኞቹ እየሰጠ ነው፡፡ በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ሹመት ሥልጠናው ያስፈለገበትን ምክንያት በመጥቀስ ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን በዚህም ሰራተኛው መብትና ግዴታውን አውቆ ስራዎችን እንዲሰራና የተመደበበትን የስራ መደብ በአግባቡ እንዲወጣ በማሰብ የተዘጋጀ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ይህ ሥልጠና በዋናነት በተለያዩ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደሚሰጥ የተናገሩት አቶ አበበ በዚህም በሰራተኞች መካከል ያለው የስራ ግንኙት ምን መምሰል እንዳለበት ይዳሰሳል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሥልጠናው የስራ ቅጥር፣ የደረጃ እድገት፣ ዝውውር፣ የብቃት ማረጋገጫ ሥርዓት፣ ደሞወዝ፣ የስራ ድልድል፣ መዋቅራዊ አደረጃጀትና መሰል ተግባራት የሚቃኙበት ሲሆን የተቋሙ ሰራተኞች በስራ ቦታ ላይ ለሚፈጠሩ ክፍተቶችና ሥራን በአግባቡ አለመወጣት ተጠያቂነትን እደሚስከትል በመገንዘብ መብታቸውን ደግሞ በአግባቡ እንዲተገብሩ በማሰብ የተዘጋጀ ነው፡፡ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በተቋማዊ ለውጥ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳው አስረስ ተዘጋጅቶ ለስልጠናው መነሻ የሚሆን የመወያያ ሰነድ የቀረበ ሲሆን በተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናን መነሻ በማድረግ ከሰራተኞች ጋር ሰፊ ውይይት የሚደረግ ይሆናል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(የካቲት 17/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት አርባ ለሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ዓቃቢነ - ሕግ ሥልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ በስልጠናው ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ተክሌ በዛብህ በንግግራቸው ኢንስቲትዩቱ በየዓመቱ የሚደርግላቸውን የስልጠና ድጋፍ በማመስገን የጀመሩ ሲሆን በመሆኑም ይህ ዕድል የተመቻቸላቸው ሰልጣኞች ሥልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ተግባር ላይ ያውሉት ዘንድ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡ በሚንስቴር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በመክፈቻ ንግግራቸው በአንድ ወቅት በአለም ባንክና ሌሎች ተቋማት በተጠና ጥናት የፍትሕ ዘርፉ ትልቁ ችግር የማሰልጠኛ እጥረት መኖሩ፣ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር የሚሰራ ተቋም አለመኖሩ እንደሆነ ተጠቆመ፤ ይህንን መነሻ በማድረግ የያኔው የፍትሕ አካላት ምሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የአሁኑ የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት በሚል ስያሜ ተጠሪነቱ ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሆኖ ይገኛል ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ተቋሙ የተቋቋመባቸውን አራቱ መሰረታዊ ፒላሮች ማለትም ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ማድረግ፣ የፍትሕ አካላትን አቅም ማጎልበት፣ የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያዎችን መደገፍ እና የሃገሪቱ ህግና ፍትሕ መረጃ ማዕከል ሆኖ ማገልገል እንደሆነ የጠቀሱት ሚንስቴር ዴዔታው በመሆኑም ይህ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በበጀት ዓመቱ ሊሰሩ ከታቀዱ ሥራዎች ውስጥ የተቀመጠና የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ተደርጎበት የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡ ስልጠና በራሱ ግብ አይደለም፤ በመሆኑም የሰለጠናቹህትን ሥልጠና ለሌሎች ባልደረቦቻቹህ በማካፈል የታለመለትን ዓላማ ከግብ ልታደርሱ ይገባል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ስልጠና በአምስት የተለያዩ ዙሮች 200 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ አቃቢነ ሕግ እንደሚሰለጥኑት ተናግረዋል፡፡ ስልጠናው የኮንስትራክሽን ሕግ፣ የፍታብሔር ሥነ-ስርዓት ሕግ፣ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ፣ የዓቃቢነ-ሕግ ሙያዊ ሥነምግባር፣ ለህዝብ ጥቅም ሲባል ስለሚለቀቅ ንብረት፣ በይዞታ መሬት ላይ የሚነሱ ክርክሮች አድማስ፣ እና መሰል ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሚሰጥ ነው፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(የካቲት 13/2017 ዓ.ም) የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የፌዴራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት መስቀል ፍላወር ቅጥር ግቢ በመገኘት የሥራ ጉብኝት አደረጉ፡፡ ፕሬዝደንቱ በሥራ ጉብኝታቸው ወቅት ለሠራተኞች ምቹ የሥራ አካባቢን ከመፍጠር አኳያ፣ ለዳኝነትና ለፍትሕ አካላት ሰልጣኞች እና አሰልጣኞች ምቹ የሥራ ከባቢንና መሰረተ ልማት ከማሟላት እና ሳቢ እንዲሆን በማድረግ አኳያ የሚታዩ ክፍተቶችን የተለያዩ ክፍሎችን በመዘዋወር የጎበኙ ሲሆን በዚህም መስተካከልና መወሰድ ስላለባቸው ጉዳዮች ከኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሰልጣኝ ማደሪያ ክፍሎች ደረጃቸውን እንዲጠብቁ ከማድረግ፣ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን ከማካሄድ፣ ሁሉን አቀፍ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በብቁ አሰልጣኞች ከመስጠት፣ የሕግ ፖርታል ዌብሳይት እና የፍትሕና ሕግ መረጃ ማዕከልን ከማጠናከር ረገድ፣ የኢ-ለርኒንግ ሥርዓቱን ሥራ እንዲጀምር ከማድረግና የማሰልጠኛ ሞጁሎችን ከማዘጋጀት አኳያ ሰፊ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ በጉብኝቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረትን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ለወደፊት ሰፊ ሥራ መስራት የሚቻልና ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች መኖራቸው ግንዛቤ ተወስዷል፡፡ ዳኞች ነፃና ገለልተኛ በሆነ ተቋም እንድሰለጥኑ ለማድረግ የፌዴራል ሕግና ፍትህ ኢንስቲትዩት የተጠሪነት ጉዳይ በቅርብ ጊዜ በሕግ አውጪው ምክር ቤት ማቋቋሚያ ሕጉን በማሻሻል መፍትሔ የተሰጠው ሲሆን ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲሆን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(የካቲት 13/2017 ዓ.ም) በዕለቱ ኢንስቲትዩቱ ውስጥ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮቶችን በመዘዋወር ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር ተጀምረው ያልተጨረሱና በሁለተኛው ፌዝ መሰራት ስላለባቸው ጉዳዮች የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ኢንስቲትዩቱ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ዘርፉ ተዋናዮችን ብቻ ሳይሆን የክልል ዳኞች፣ ዓቃቢ - ህግ እና ፖሊሶችን ጭምር እንደሚያሰለጥን ከቀረበው ሰነድ የተነገረ ሲሆን ማሰልጠኛው ከመሃል ከተማ ራቅ ያለና ከሃያ ኪሎ ሜትሮች በላይ መራቁ ለስራ እንቅፋት እየሆነ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የትራንስፖርት ጉዳይ ሌላው ለስራ እንቅፋት እየሆነ የመጣ ጉዳይ ነው የተባለ ሲሆን ይህም አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚስፈልገው ነው የተጠቆመው፡፡ በሰነዱ እንደተጠቆመው የአውሮፓ ህብረትና የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት አብረው ሊሰሩ ከተስማሙባቸው ጉዳዮች መካከል የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ አብሮ መስራት፣ ጥራት ያለውና ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ፣ ለዳኞችና ለፍትሕ ስርዓቱ ተዋናዮች አቅም ግንባታ መስጠት፣ የሃገሪቱ ፍትሕና ሕግ መረጃ ማዕከል ግንባታና እና ኢ-ለርኒግ ላይ አብሮ ለመስራት የተነጋገሩ ሲሆን መሰረተ ልማቶችን ከማሟላትና መሰል ተግባሮችን ከመፈጻም አኳያ ደግሞ ህብረቱ ወደፊት በአንክሮ ሊሰራባቸው እንዳሰበ ተነግሯል፡፡ በዕለቱ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች፣ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ኤች.ኢ ሶፊ እና የሕብረቱ አመራሮች እንዲሁም ከገንዘብ ሚንሰቴር ከፍተኛ ባለሙያዎች ተገኝተው ነበር፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(የካቲት 11/2017 ዓ.ም) ትናንት በቦንጋ ከተማ መሰጠት የጀመረው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ፖሊሶች ሥልጠና ዛሬም እንደቀጠለ ነው! በዘህ ስልጠና ከተያዙ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የወንጀል ስፍራ ማስረጃ አሰባሰብ አንዱ ሲሆን በዚህ ላይ የተመረኮዘ በአስገድዶ መድፈርና የሞት ወንጀል ላይ የተመረኮዘ ተግባር ተኮር የወንጀል ስፍራ መረጃ አሰባሰብን ሲለማመዱ ውለዋል፡፡ ይህንን ተግባር ተኮር የመረጃ አሰባሰብ በተወሰነ መልኩ በፎቶ እና በቪዲዮ አስቀርተነዋል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(የካቲት 11/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቦንጋ ከተማ ትናንት መስጠት የጀመረው የፍትሕና ሕግ ዘርፍ ስልጠና ዛሬም እንደቀጠለ ነው! በዕለቱ ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉት የተወካዮች ምክር ቤት አባልና በሚኒስቴር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው ኢንስቲትዩቱ የተቋቋመበትን አራት ዓላማዎች ለሰልጣኞች በመንገር የጀመሩ ሲሆን በዚህም ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ፣ ለፍትሕና ሕግ ዘርፉ አስፈላጊውን ሥልጠና ማመቻቸት፣ የፍትሕና ሕግ ሥርዓት ማሻሻያዎችን መደገፍ እና አገር አቀፍ የፍትሕና ሕግ መረጃ ማዕከል ሆኖ ማገልገል ተቀዳሚ ተግባራቶቹ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ ህዝቡ በርካታ የፍትሕ ጥማት አለበት፤ በመሆኑም የህብረተሰቡን የፍትሕ ጥያቄ ለመመለስ ዳኞች፣ አቃቤ ህግ እና ፖሊሶች ተደራጅተው በተናበበና በተጠና መልኩ ስራዎችን መስራት አለባቸው ያሉት ሚኒስቴር ዴዔታው ለዚህም መነሻ ይሆን ዘንድ ይህ ስልጠና ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡ የፍትሕ ሥርዓቱ ጠንካራ ሲሆን አገር ትጠናከራለች ያሉት አቶ ዘካርያስ ይህ መሆኑ ደግሞ በህዝብና በመንግስት መካከል መተማመንና መግባባትን ይፈጥራል ብለዋል፡፡ በዚህ ስልጠና 40 ዳኞች፣ 40 ዓቃቢነ - ህግ እንዲሁም 40 ደግሞ መርማሪ ፖሊሶች የተካተቱ ሲሆን ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሚሰጥ ነው!

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(የካቲት 11/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ፍትሕና ሕግ ባለሙያዎች በተለያዬ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ነው፡፡ ስልጠናው በዋናነት ዳኞች፣ አቃቢነ-ህግ እና ፖሊሶች ላይ ትኩረት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እየጠሰጠ ነው፡፡ በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ቆጭቶ ገ/ማርያም በንግግራቸው ክልሉ እስካሁን የፍትሕና ሕግ አካላት ማሰልጠኛ ተቋም እንደሌለው በመጥቀስ በመሆኑም ባለፈው ዓመትም ሆነ በዚህ ስልጠና የክልሉን ፍትሕና ሕግ ዘርፍ በማሰልጠንና በማብቃት ረገድ የፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለሚያደርገው ቀና ትብብር ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡ ስልጠናውን በጥብቅ የስራ ሥነ-ምግባር ተከታትለን ማጠናቀቅ አለብን ያሉት ፕሬዚዳንቱ ነገር ግን ሥልጠና በራሱ ደግሞ ግብ አይደለምና ከዚህ ሥልጠና የምናገኘውን ዕውቀት፣ ክህሎት እና የአመለካከት ለውጦችን በስራችን ላሉ ባለሙያዎች ማካፈልና ተደራሽ ማድረግ አለብን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ስልጠናው በተጨባጭ ከአጋጠሙ ነገሮች በነመሳት ተግባር ተኮር የሆነ ይዘትን የተላበሰ ሲሆን ለዳኞች የጦር መሳሪያ ሕግ፣ የፌዴራል ታክስ ሕግ፣ የዳኝነት ስልጣንና የመሬት ካሳ ሕግ ላይ ተመርኩዙ፣ የአቃቢያነ - ሕግ የሥልጠና ርዕሶች የኮንስትራክሽን ሕግ፣ የዓቃቢነ - ሕግ ሥነ-ምግባር እና የሙስና፣ የታክስና ኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎች ላይ በማተኮር እንዲሁም የፖሊሶች ሥልጠና ደግሞ የወንጀል ስፍራ ማስረጃ አሰባሰብ፣ የወንጀል ምርመራ ሳይንስ ክህሎት እና የኤሌክትሮኒክስ መሳሪዎችን በመጠቀም የሚፈጸሙ ወንጀሎች ምርመራ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

ዜና

(ጥር 29/2017 ዓ.ም) ምክር ቤቱ ሁለት አዋጆችን አፀደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 18ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌደራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት እንዲሁም የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ ስርዓት አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል፡፡ የፌደራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም በህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 1000 /369/2017 ሆኖ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል፡፡ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ማዕከል ያደረገ ጥናትና ምርምር በማድረግ የዳኝነትና የፍትህ ስርዓቱን ማዘመን፣ ህጎችን ከወቅታዊው የዓለምና የሀገሪቱ የእድገት ደረጃ እንዲጣጣም ለማድረግ ጠንካራ የህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱም አዋጁ ወጥቷል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም ምክር ቤቱ የሚወጡ አዋጆች ላልተፈለገ አላማ እንዳይውሉና ጥንቃቄ እንዲደረግ በማሳሰብ የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ ስርዓትን ለመደንገግ የወጣ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አዋጁን በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ጥር 17/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የ6 ወር ስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ዛሬ በአዳማ ከተማ ለሰራተኞቹ አቀረበ፡፡ በዚህም ተቋሙ ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ እቅድ አውጥቶ ወደ ስራ መግባቱ የተነገረ ሲሆን ባለፉት ስድስት ወራት የተቋሙ እና የስራ አስፈጻሚዎች የስራ አፈጻጸም፣ የበጀት አጠቃቀምና መሰል ጉዳዮች ቀርበው መድረኩ ለውይይት ክፍት ተደርጓል፡፡ በዚህ መሰረት ሰራተኞቹ በዕለት ከዕለት የስራ እንቅስቃሴያቸው የሚጋጥሟቸውን ችግሮች በማንሳት ለከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮቹ ሃሳባቸውን አጋርተዋል፡፡ ከእነዚህ ተግዳሮቶች መካከል በሁለቱም የተቋሙ ህንጻዎች ላይ የሚገኙ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለምሳሌ የውሃ፣ የመብራት፣ የትራንስፖርት፣ የህጻናት ማቆያና መሰል ጉዳዮች አፋጣኝ መፍትሄ ሊበጅላቸው እንደሚገባ ነው የተጠቆመው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ስራዎቻችን የተቋሙን ሰራተኞች በአማከለ መልኩ ተሰርተው ወቅታቸውን ጠብቀው ለሚመለከተው አካል መድረስ እንዳለባቸው የተነገረ ሲሆን በሕግና መመሪያ የተመራ አስተዳደር እንዲኖር ያሻል ተብሏል፡፡ በዕለቱ ንግግር ያደረጉት በሚንስቴር ማዕረግ የፌዴራል የፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በንግግራቸው ይህ የጋራ መድረክ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት ሁሉም ሰራተኛ በተቋሙ ላይ እኩል ግንዛቤ እንዲኖረው በማስፈለጉ ነው ያሉ ሲሆን ይህ መሆኑ ደግሞ ተቋማችን፣ ሥራ አስፈጻሚዎችና ሰራተኞች ያሉበትን ሁኔታ በሚገና በመገንዘብ እያንዳንዱ ሰራተኛ የተሰጠውን ሥራ በአግባቡ ሰርቶ ማስረከብ እንዳለበት ለማሳወቅ ጭምር የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡ ከቤቱ የተነሱ ጉዳዮች መካል የህጻናት ማቆያና የመብራ መቆራረጦች በቅርቡ መፍትሄ ያገኛሉ ያሉት አምባሳደሩ ሌሎች ጉዳዮችን ደግሞ ከከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጋር በመወያዬት ወቅታቸውን ጠብቀው መፍትሄ እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በዚህም ከሰራተኞች የተነሱ የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በመካከለኛና በበላይ ሃላፊዎች ምላሽ የጠሰጠባቸው ሲሆን የ6 ወር አፈጻጸም ሪፖርቱን ደግሞ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ዋቅጋሪ አቅርበውታል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ጥር 16/2017 ዓ.ም) የሰራተኞች መልካም ግንኙነት ለተቋም ውጤታማነት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና በሚንስቴር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካሪያስ ኤርኮላ ተናገሩ፡፡ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን የተናገሩት የፌዴራል የፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት የሰራተኞች ግንኙነት፣የግጭት አፈታት፣ ሰነድ አያያዝና የቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ሥርዓት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለሰራተኞቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና እየተሰጠ ባለበት ወቅት ነው፡፡ በዕለቱ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተከበሩ አቶ ዘካሪስ ምንም እንኳን በዕለት ከዕለት እንቅስቃሴዎቻችን ግጭቶች ቢጋጥሙንም ችግሮቹ ሥር ሳይሰዱ መፍታት የሚቻልበትን መንገድ መቀየስና ፊት ለፊት መነጋገር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ የዘለለ ጉዳይ ከሆን የቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ስርዓታችንን በማዘመን ችግሮቻችን አፋጣኝ መፍትሄ እንዲኖራቸው ማድረግ አለብን ያሉት ሚንስቴር ዴዔታው በተጨማሪ ተቋማዊ የሰነድ አያያዛችን መስተካከልና ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ የመወያያ ሰነዶቹ በብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ አቶ መርሹ ዘለቀ እና በተቋማዊ ለውጥ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳው አስረስ ቀርበው ለውይይት የበቁ ሲሆን ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሃሳብና አስተያዬቶች ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋ፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ጥር 13/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የሕግ ጥናትና ምርምር አውደ ጥናት ዛሬ አካሄደ፡፡ በአውደ ጥናቱ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በሚንስቴር ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በንግግራቸው ኢንስቲትዩቱ ከተሰጡት ተግባርና ሃላፊነቶች መካከል አንዱ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ማካሄድና ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ ሕግ ሆኖ እንዲወጣ አልያም ደግሞ ለፖሊሲዎች ግብዓት መስጠት ነው በማለት ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን ጥናቶች በዋናነት የፌዴራል፣ የክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የፍትሕና ሕግ ነክ ጉዳዮችን ትኩረት በማድረግ ይሰራሉ ብለዋል፡፡ ይህንንም መሰረት በማድረግ የዛሬው የሕግ ጥናትና ምርምር አውደ ጥናትም በፌዴራልና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህና ሕግ ነክ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገዋል ያሉት አምባሳደሩ አምስት ጥናትና ምርምሮች ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንደሚቀርቡም መረጃ ሰጥተዋል፡፡ በዕለቱ የአስተዳደር ወሰን ሕግ ማዕቀፍ በኢትዮጵያ፡-የአስተዳደር ድንበር ግጭት መፍቻ ስልቶች፣ ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎች፣ በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ጥናት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጎጂዎች የሚካሱበት የሕግ ማዕቀፍ እና የአሰራር ሥርዓትን በተመለከተ የተደረገ ጥናት፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 የሕግ ማዕቀፍና አተገባበር እና የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሥልጣን፣ የሥልጣን ተዋረድ እና ግንኙነት የሚሉ አምስት የተለያዩ ጥናቶች ለባለድርሻ አካላት ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ታህሳስ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለመከላከያ ፍርድ ቤት ዳኞች በአዲስ አበባ ከተማ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ በዕለቱ በስልጠናው ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና በሚኒስቴር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍትህ እና የህግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው የፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የሚሰጣቸውን አንኳር ተግባራት በመጥቀስ ለሰልጣኞቹ የተናገሩ ሲሆን ከእነዚህም ተግባራት መካከል ሁሉንም የፍትሕ አካላትን በስልጠና የማብቃት፣ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ፣ የፍትህ ሥርዓት ማሻሻያዎችን መከታተልና የሃገሪቱ ፍትሕና ሕግመረጃ ማዕከል ሆኖ ማገልገል እንደሆነ ተናግረዋል፡ ሁሌም እንደምለው እድሜያቸው የሚፈቅድላቸው ዜጎች የወታደራዊ ዲሲፕሊን ስልጠናዎችን ለሁለት አመት መከታተልና ማገልገል ይጠበቅባቸዋል ያሉት ሚንስቴር ዴዔታው ይህንን ማድረግ አለመቻሌ እስካሁን ድረስ ይቆጨኛል ሲሉ ተናግረዋል። ስልጠና በራሱ ግብ አይደለም፤ ያሉት የተከበሩ አቶ ዘካሪያስ በመሆኑም የምናገኛቸውን ስልጠናዎች ወደ ተግባር በመለወጥ የህብረተሰቡን የፍትሕ ጥማት ማስታገስ አለብን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሚኒስቴር ዴዔታ ማዕረግ የመከላከያ አግሮ ፕሮሠሲንግ አስተባባሪ ክቡር አቶ ቶማስ ቶት በበኩላቸው የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በአመት ሁለት ጊዜ ለመከላከያ ሚንስቴር የህግ ባለሙያዎች እየሰጠ ያለውን ስልጠና በማድነቅ ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን በዚህም እነዚህንና መሰል ስልጠናዎች በዘርፉ ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን ለመድፈን የሚግዙ በመሆናቸው ለተደረገልንም ሆነ ለሚደረግልን ቀና ትብብር እናመሠግናለን ብለዋል፡፡ እነዚህ አይነት ስልጠናዎች ሰራዊታችን በተለያዩ አጋጣሚዎች ለሚኖረው ግዳጅ ሚናቸው የጎላ ነው ያሉት ሚንስቴር ዴዔታው በመሆኑም እዚህ ለመስልጠን እድል የገጠመን ሰልጣኞች በምንመለስበት የስራ ቦታ ሌሎችን ማብቃትና ተገማችና ታማዓኒ የሆነ የሕግ ውሳኔ መስጠት አለብን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለሚቀጥሉት አምስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን የወንጀል ሕግ መርህ ከወታደራዊ ሕግ አንፃር፣ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ 2/2006 እና የወንጀል ስነ ስርዓት ሕግ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን የሚያደርግ ይሆናል ።

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በአዳማ ከተማ ሲካሂድ የቆየው የመጀመሪ ዙር የቅድመ ሥራ ስልጠና ትምህርት (ካሪኩለም) ክለሳ ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ በቅድመ ሥራ ስልጠና ትምህርት (ካሪኩለም) ክለሳው ላይ ከፌዴራል ከፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የተወጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የቅድመ ስራ ስልጠና የጀመሩ የክልል ፍትሕና ሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩቶች የተሳተፉ ሲሆን ላለፉት ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ ይህ ክለሳ በቀጣይ ለሁለተኛና ለሶስተኛ ዙሮች የሚካሄድ ሲሆን በተቀመጠለት የጊዜ ቅድመ ተከተሎች የሚደረግ ይሆናል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ታህሳስ 17/2016 ዓ.ም)የፌዴራል የፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት በአዳማ ከተማ እያካሄደው የሚገኘውን የቅድመ ሥራ ስልጠና ስርዓተ ትምህርት (ካሪኩለም) ክለሳ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡ ይህንን በሚመለከት የኢንስቲትዩቱ የፍትሕ ስርዓት ማሻሻልና የህግ መረጃ ማዕከል መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አረጋ ሱፋ በሰጡት ማብራሪያ የሕግ የቅድመ ሥልጠና ሥርዓተ ትምህርት  ክለሳ  ያስፈልገበት  ዋና ዋና  ምክንያቶች መካከል አሳሪ የሆኑ ሕጎች እየተሻሻሉ መምጣታቸው ፣ የስልጠና  አሰጣጥ ዘዴ ሠልጣኝ ተኮር መሆን ስላለባቸው  እንዲሁም በአገራችን የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ  ለውጦች  መምጣታቸውን መሠረት በማድረግ የሕግ  የቅድመ ሥልጠና ሥርዓተ ትምህርት በመከለስና በማሻሻል የስልጠና ጥራትን ለማስጠበቅ የሚረዳ ቁልፍ ተግባር  እንደሆነ በመግለፅ በአጠቃላይ የሕግ የቅድመ ሥልጠና ሥርዓተ ትምህርት  ክለሳ አስፈላጊ የሚሆንባቸው አንዳንድ  ምክንያቶችን ለመዳሰስ ያህል  ማህበረሰቦች በፍጥነት እየተለወጡ መምጣታቸው  ፣ የቴክኖሎጂ፣ የግሎባላይዜሽን እና የማህበራዊ እሴቶች ለውጥ ሁሉ የሕግ ስርዓቱን እንዲያጠናክሩ ይጠበቃሉ ብለዋል። ለምሳሌ እንደ ሳይበር ወንጀል፣ የሰው አካል ንግድ እና የአካባቢ ጥበቃ ያሉ አዳዲስ የሕግ ጉዳዮች በቅድመ ስልጠና  ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ  መካተት አለባቸው ያሉት አቶ አረጋ በሌላ መልኩ የሥራ ገበያ ፍላጎቶች በየጊዜው እየተለወጡ መምጣታቸው፣ እየተበራከቱ የመጡ ኢንዱስትሪዎች  በተለያዩ ዘርፎች የሰለጠኑ  ሰራተኞችን በመፈለጋቸው፣ የሕግ ስርዓቱም ለዚህ ለውጥ ምላሽ መስጠት ይጠበቅበታልና  በሂደት የንግድ ሕግ ፣ የአካባቢ ጥበቃ ሕግ እና የሰብአዊ መብቶች ሕግ ላይ ያተኮሩ ተጨማሪ  የስልጠና ኮርሶች  የቅድመ ሥልጠና ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ  መጨመር  ስላለባቸው የሚደረግ ክለሳ ነው ብለዋል። በተጨማሪም የስልጠና  አሰጣጥ ዘዴዎችን  በከፍተኛ ደረጃ  ማሻሻል  ይጠበቅብናል ። ለአብነት  በስልጠናው  ሂደት ሰልጣኞች ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉበት ፣ ችግርን የመፍታት ክህሎትን የሚያዳብሩበትና እና በቡድን የመሥራት ችሎታን የሚያሳድጉበት የስልጠና  አሰጣጥ  ዘዴዎች ተወዳጅ መሆን አለባቸው ያሉት መሪ ስራ አስፈፃሚው የሕግ ስልጠናም ከዚህ አጠቃላይ አዝማሚያ ውጭ መሆን አይችልም ሲሉ አብራርተዋል። በመጨረሻም የስልጠና መርሃ ግብሮችን በየጊዜው ማሻሻል  ወሳኝና  አስፈላጊ  ጉዳይ ነው  ።  የስልጠና መርሃ ግብሮች በየጊዜው በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ቴክኖሎጂያዊ ለውጦችን መሠረት በማድረግ መሻሻል አለባቸው ። ስለዚህ የሕግ የቅድመ ሥልጠና ሥርዓተ ትምህርት ክለሳ በየ 5 አመቱ  የሚደረግ ቀጣይነት  ያለው ሂደት ነው ።  ይህ ሂደት ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ቴክኖሎጂያዊ ለውጦችን ማዕከል በማድረግ የወደፊቱን የሥራ ገበያ ፍላጎቶችን ለማሟላት አስፈላጊ ነው ። ከዚህ አኳያ  አዳዲስ እውቀቶችን ፣ ክህሎቶችንና በተግባር ተኮር  ስልጠና እየገነቡ ብቃት ያላቸው የሕግ ባለሙያዎችን ማፍራት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ  ነው በማለት ንግግራቸውን አጠቃለዋል።
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የቅድመ ሥራ ስልጠና ትምህርት (ካሪኩለም) ክለሳ ዛሬ በአዳማ ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡ ይህ የመጀመሪ ዙር የቅድመ ሥራ ስልጠና ትምህርት (ካሪኩለም) ክለሳ ሃገራዊ ከመሆኑ ባሻገር በተሸሩ ሕጎች ምትክ የሚሻሻሉ ሕጎች ስለሚኖሩ፣ አዳዲስ የሚመጡ ሕጎች የሥርዓተ ስልጠናው አካል መሆን ሥለሚገባቸውና ከአገራዊና ዓለም አቀፋዊ አዳዲስ የሕግ ለውጦች ጋር የተጣጣመ ሥርዓተ ሥልጠና እንዲዘረጋ ስለሚያስፈለግ የሚደረግ ክለሳ ነው፡፡ የቅድመ ሥራ ስልጠና ትምህርት (ካሪኩለም) ክለሳው በዋናነት በኢንስቲትዩቱ የህግ ባለሙያዎች ምዘና እና ብቃት ማረጋገጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ የሚመራ ሆኖ ከፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት አመራርና ባለሙያዎች እና የቅድመ ሥራ ስልጠና እየተገበሩ ካሉ የክልል የፍትሕና ሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩት ተወካዮች ጋር እየተደረገ ይገኛል፡፡ በካሪኩለም ክለሳው ላይ ተገኝተው ሃሳባቸውን ያካፈሉን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፍትሕና ሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩት ተወካይ አቶ አለሙ ያዴሳ በንግግራቸው የስልጠና ካሪኩለም የስራቸው ሮድ ማፕ መሆኑን በመጥቀስ ባለፈው ዓመት ውይይት እንደተደረገበትና ሃገራዊና ወጥ የሆነ የሥልጠና ሥርዓት መገንባት አስፈላጊ እንደሆነ የጋራ መግባባት እንደተደረሰበት የተናገሩ ሲሆን ይህም በየትኛውም ክልል የሰለጠነ የሕግ ባለሙያ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተንቀሳቅሶ እንዲሰራ ያግዘዋል ብለዋል፡፡ በክልሎች ላይ ልዩነት የሚፈጥሩ የስልጠና ሥርዓቶችን በማጤን አንድ አይነት የስልጠና ሥርዓት መዘርጋት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ሃላፊነት ነው ያሉት አቶ አለሙ ይህንንም ከግምት ውስጥ በማስገባት የስርዓተ ሥልጠና ክለሳ መጀመሩን አመስግነዋል፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

ቋሚ ኮሚቴው የፌዴራል ፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል። የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወይዘሮ እፀገነት መንግሥቱ የፌዴራል ፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱ ተቋሙ ውጤታማ እንዲሆን የሚረዳው መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም፣  አዋጁን  አዳብሮ በማውጣት ለረጅም ጊዜ የሚያሠራና ችግር የሚፈታ በማድረግ ኢንስቲትዩቱ ውጤታማ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገው ውይይት የተገኘውን ግብዓት በመጠቀም ቋሚ ኮሚቴው ረቂቅ አዋጁን በድጋሚ የሚመረምረው መሆኑን ተናግረዋል። ሰብሳቢዋ አክለውም፣ ኢንስቲትዩቱ ሁሉንም የፍትህና የዳኝነት አካላት እኩል እንዲያገለግል፣ በእውቀትና በክህሎት በተገነባ የሰው ኃይል እንዲጠናከር፣ ተቋሙ  ኃላፊነቱን እንዲወጣ ለማድረግ የረቂቅ አዋጁ መዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። ኢንስቲትዩቱ በሚያደርገው ጥናትና ምርምር እንዲሁም በሚሰጠው ሥልጠና የፍትህና የዳኝነት አካላትን ችግር በትክክል ለመፍታት፣ ኢንስቲትዩቱን እንደገና ለማቋቋምና ለማደራጀት አዋጁን እንደገና ማውጣት ማስፈለጉን የተከበሩ ወይዘሮ እፀገነት መንግሥቱ ጨምረው አብራርተዋል። የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ኢሳ ቦሩ በበኩላቸው፣ ቋሚ ኮሚቴው ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ለማዘጋጀት የሚያስችል ጠቃሚ ግብዓቶችን ማግኘቱን ተናግረዋል። የፌዴራል ፍትህና ሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በሰጡት አስተያየት፤ ከተወሰኑ ክልሎች በስተቀር አብዛኞቹ ክልሎች የፍትህና የዳኝነት አካላት የጥናት፣ የምርምርና የማስልጠኛ ኢንስቲትዩት ስለሌላቸው በፌዴራል ደረጃ የሚቋቋመው ኢንስቲትዩት በማዕከል በሚያደርገው ጥናትና ምርምር እንዲሁም በሚሰጠው ሥልጠና በሁሉም ክልሎች ያሉ የፍትህና የዳኝነት አካላትን ተጠቃሚ ሊያደርግ እንደሚችል አብራርተዋል፡፡ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ አሮን ደጎል ለውይይት መነሻ የሚሆን ጽሑፍ ከቀረበ በኋላ ለውይይት ከመጡ ባለድርሻ አካላት በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው በኢንስቲትዩቱ የሥራ ኃላፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል።

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ሕዳር 21/2017 ዓ.ም) ከትናንት ጀምሮ በአዳማ ከተማ የተካሄደው የ2017 በጀት ዓመት የሕግ ትምህርት ቤቶች ኮንሰርቲየም የመጀመሪያ ዙር ዓመታዊ ስብሰባ ዛሬ ፍጻሜውን አገኘ፡፡ በስብሰባው በተያዘው በጀት ዓመት የምስለ ችሎት ውድድርና የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ አዘጋጅ ዩንቨርሲቲዎች የተመረጡ ሲሆን በዚህም ቦረና ዩንቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንሱን ለማዘጋጀት፣ ሚዛን ቴፒ ዩንቨርሲቲ ደግሞ የምስለ ችሎት ውድድር አዘጋጅ በመሆን ተመርጠዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመማሪያ ሞጁል አዘጋጅ ኮሚቴ፣ የእውቅና እና ሽልማት እንዲሁም የስልጠና መመሪያዎች አዘጋጅ ኮሚቴ የተመረጠ ሲሆን ሌሎች ኮሚቴዎች ባሉበት እንዲቀጥሉ ተደርጓል፡፡ በፕሮግራሙ ማጠናቀቂያ ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት በፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያና የሕግ መረጃ ማዕከል መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አረጋ ሱፋ በንግግራቸው ተሳታፊዎች ለነበራቸው ቆይታ በማመስገን የተመረጡ ኮሚቴዎችም ሆኑ አዘጋጅ ዩንቨርሲቲዎች የተሰጣቸውን ተግባርና ሃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

((ሕዳር 20/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የ2017 በጀት ዓመት የሕግ ትምህርት ቤቶች ኮንሰርቲየም የመጀመሪ ዙር ዓመታዊ ስብሰባ በአዳማ ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡ በስብሰባው ማስጀመሪ ዕለት የእኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የፌዴራል የፍሕና የሕግ አንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው ኮንሰርቲየሙ የመጀመሪ ስብሰባው እንደሆነ በመጥቀስ በዚህ ስብሰባም ቀጣይነት ያለውና ለትውልድ የሚሸጋገር ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ መልዕክታቸውን አስተላፈዋል፡፡ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዕለቱ የክብር እንግዳና የፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በንግግራቸው የሕግ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎቻቸው የሚስፈልጋቸውን ዕውቀት ሰጥተው ይሸኟቸዋል፤ እኛ ደግሞ በክህሎትና በስነ ምግባር ማነጽ ይጠበቅብናል ያሉ ሲሆን ይህም ኢንስቲትዩቱ ከህግ ትምህርት ቤቶች ጋር ያለውን ቅብብሎሽ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡ ስብሰባው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ከሆኑት የሕግ ትምሕርትና ሥልጠና ማሻሻያ ፕሮግራም የ2016 በጀት አፈጻጸምና የ2017 በጀት ዓመት የወደፊት አቅጣጫዎች፣ የህግ መማሪያ ሞጁሎች ዝግጅት ያሉበት ሁኔታ፣ የሕግ ትምህርት ቤቶች መዋቅር ጥናት በተመለከተ ውይይት ማድረግና የእውቅና እና ሽልማት ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ኢሜል:- pr@fjli.gov.et
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ሕዳር 19/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በዓለም ለ33ኛ ጊዜ እንደ ሃገር ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ የሴቷ ጥቃት የኔም ነው ዝም አልልም በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የነጭ ሪቫን ቀን አክብሮ ውሏል፡፡ በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በንግግራቸው የነጭ ሪቫን ቀን ሁላችንም ቆም ብለን ወደ ራሳችን እንድናይ የሚያደርግ ቀን ነው ያሉ ሲሆን በተለይ ጦርነትና ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች በአብዛኛው የሚጠቁት ሴቶችና ህጻናት በመሆናቸው ከእነርሱ ጎን ሆነን የሚቻለንን ሁሉ ልናደርግላቸውና ልንደግፋቸው ይገባል ብለዋል፡፡ ተቋማችን የፍሕና ሕግ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ከሌሎች ተቋማት በተለዬ መልኩ አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት ያሉት አምባሳደሩ ሴቶችና ሕጻናት ላይ ትኩረት ያደረጉ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ፣ በስልጠና ደግሞ የእኩል ተጠቃሚነትና ለሰልጣኞች የሴቶች ጥቃትን በሚመለከት ግንዛቤ መስጠት ላይ ልንሰራ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በዕለቱ የነጭ ሪቫንና የሴቶች ጥቃት ላይ ትኩረቱን ያደረገ የመወያያ ሰነድ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ተወካይ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መቅደስ ሕዝቅኤል የቀረበ ሲሆን ይህንንም መሰረት በማድረግ ተሳታፊዎቹ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡ የነጭ ሪቫን ቀን ማለት በተለያዩ ሥራ ቦታዎች ስነ-ምግባር የጎደላቸው ወንዶች በሴቶች ላይ የሚፈጽሙት ዖታዊ፣ ሥነ-ልቦናዊና አካላዊ ጥቃትን ለመከላከል ያለመ ቀን ሲሆን ዋና ዓላማውም ወሲባዊ ትንኮሳ እና ማስፈራራትን ማስቆም ነው፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

ትናንት ህዳር 18 ቀን፣  2017 ዓ.ም፤ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ እና ሕግ ኢኒስቲትዩትን እንደገና ለማሻሻል በወጣው ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ከኢንስቲትዩቱ እና ከጠቅላይ ፍ/ቤት ከመጡ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል። ረቂቅ አዋጁ ኢንስቲትዩቱን ይበልጥ እንዲያጎለብተውና ሥራዎችን በዘላቂነት ሊያሰራው በሚችል መልኩ እና ለረጅም ዓመታት እንዲያገለግል ትኩረት መሰጠቱን ቋሚ ኮሚቴው አስረድቷል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ አርትኦቱን ጨምሮ ማሻሻያና ማስተካከያ የሚደረግባቸው ረቂቅ አዋጁ አንቀፆች ማስተካከያ ተደርጎባቸው ቶሎ ለቋሚ ኮሚቴው መምጣት እንዳለበት ተናግረዋል። ሰብሳቢዋ አክለውም ኢንስቲትዩቱ አሁን ከገጠመው ችግር አንፃር አዋጁ ወደ ሥራ ሲገባ እንዳያስቸግር በአግባቡ ሊያግዝ በሚችል መንገድ ድንጋጌዎቹ ተካተው መምጣት እንዳለባቸውም ነው ያስገነዘቡት። ኢንስቲትዩቱን የሚጠቅሰውን አዋጅ ንዑስ አንቀፅ ትክክለኛውን ቦታ እንዳይሳት ‹‹በነባሩ›› የሚል ነገር መጨመር እንዳለበትና እንዴት ተመራጭ ሆነ የሚለውን ኢንስቲትዩቱ ወስዶ ማስተካከል እንዳለበት የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት አስረድተው፣ ቋሚ ኮሚቴው የሚከታተላቸው ሌሎች ተቋማት አንቀፅ 98ን እንዲሻርላቸው ጠይቀው እንደተሻረላቸውና ይህ የሚሻሻለው ረቂቅ አዋጅ ለተፈፃሚነቱ አስቸጋሪ እንዳይሆን በትኩረት መታየት አለበት ብለዋል። ቦርዱን በተመለከተም የደረስንበትን ደረጃ ታሳቢ ለማድረግ ይበልጥ ሊያግዝ የሚችልና የምርምር ሥራው የሚመለከተው የሚለውን ከቋሚ ኮሚቴው ከፍ ማለት እንዳለበት ሰብሳቢዋ ገልፀው፣ የምክር ቤት አባላት ክትትል፣ ቁጥጥር እና ህግ የመመርመር ሥራ ሲሰሩ ክፍተት ስለሚኖር በቂ የሆነ የክህሎት ስልጠና ኢንስቲትዩቱ መስጠት እንዳለበትም አስረድተዋል።  ኢንስቲትዩቱን በትኩረት ለማገዝና ይበልጥ ለመደገፍ ቦርዱን እንደገና መፈተሽ እንደሚገባ ወ/ሮ እፀገነት ጠቁመው፣ የውሳኔ ሀሳብ ለመስጠት ሊያግዝ በሚችል መልኩ  መምጣት አለበት ብለዋል። የጠቅላይ ፍ/ቤት ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አቶ አሮን ዳጎል ለፍትህ ውጤታማነት እጅግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ በሚመለከታቸው አካላት የሚወጡ ህጎች ከወቅታዊ የአገሪቱ የእድገት ደረጃ ጋር የተጣጣመ ለማድረግ የረቂቅ አዋጁን አስፈላጊነት  አንስተዋል፡፡ በመጨረሻም ዳይሬክተሩ በረቂቁ ዝግጅት ዙሪያ አግባብነት ያላቸው አካላት፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት እና የፍትህ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተወያይተው ግብዓት እንደሰጡበም አብራርተዋል።

መረጃው፡- House of Peoples Representatives of FDRE
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ሕዳር 14/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በአዲስ አበባ ከተማ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ሁለተኛውን ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ፡፡ ይህ የአሰልጣኞች ስልጠና የአሰለጣጠን ዘዴ ላይ ትኩረት በማድረግ የተሰጠ ሲሆን 7 ከጠቅላይ ፍ/ቤት፣ 12 ከከፍተኛ ፍ/ቤት፣ 6 ከመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት፣ 7 ከፍትህ ሚኒስቴር አቃቢ ህጎች፣ 3 ከአዲስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ዳኞች እና 2 ከመከላከያ ወታደራዊ ፍ/ቤቶች የተወጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡ ሥልጠናው በዋናነት የአሰለጣጠን ፍላጎት ዳሰሳ፣ የስልጠና መንገዶች፣ ሰልጣኞችን ማበረታታትና የስልጠና ግምገማ ላይ ትኩረት በማድረግ ሰልጣኞችን እንዴት መያዝ እንዳለብን፣ እና ከስልጠናው በኋላ የምናገኘውን ውጤት ከግምት ውስጥ በማስገባት የተሰጠ ሥልጠና ነው፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ሕዳር 10/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ሁለተኛውን ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና በአዲስ አበባ ከተማ መስጠት ጀመረ፡፡ በስልጠናው ማስጀመሪያ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና በሚንስትር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው ይህ ስልጠና ሁለተኛ ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና (TOT) መሆኑን በመጥቀስ ይህ መሆኑ ደግሞ የወደፊት አሰልጣኞችን ለማፍራት ያለመ ስልጠና እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ሲኒየር ዳኞች ከዕለት ተዕለት ስራቸው ጎን ለጎን ጀማሪ ባለሙያዎችን ማብቃትና ማሰልጠን ይጠበቅባቸዋል ያሉት አቶ ዘካርያስ በመሆኑም ዛሬ የተገኙ የህግ ባለሙያዎች በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ ሞጁል በማዘጋጀት የአሰልጣኞች ስልጠና ሰርተፊኬት ይሰጣቸውና ሌሎች ባለሙያዎችን የማብቃት ተግባር ይሰጣቸዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የአሰልጣኞች ስልጠና በዋናነት የአሰለጣጠን ዘዴ ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰጥ ሲሆን በዚህ ሥልጠና ላይም ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ ከአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ እና ከፌዴራል የመከላከያ የተወጣጡ 40 የህግ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ይህ ሥልጠና የአሰለጣጠን ፍላጎት ዳሰሳ፣ የስልጠና መንገዶች፣ ሰልጣኞችን ማበረታታትና የስልጠና ግምገማ ላይ ትኩረት በማድረግ ሰልጣኞችን እንዴት መያዝ እንዳለብን፣ እና ከስልጠናው በኋላ የምናገኘውን ውጤት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰጥ ሥልጠና ነው፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

ዜና

የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 1ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 252361 ጥቅምት 27 ቀን 2017ዓ.ም በዋለው ችሎት ባልተከፈለ ቀረጥ እና ታክስ ላይ የሚፈለግ ወለድን አስመልክቶ በሰጠው ውሳኔ በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጲያ ባሕሎች አካዳሚ: በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕግ እና ፍትሕ ኢንስቲትዩት እና በጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎውሺፕ ኢትዮጲያ ትብብር በተዘጋጀው ዐውደ ጥበባዊ የሕግ መዝገበ ቃላት ላይ #"ወለድ" ለሚለው ቃል የተሰጠውን የሕግ ትርጉም ለመጀመሪያ ጊዜ በመጠቀም ውሳኔ ሰጥቷል። ሙሉውን የውሳኔ ይዘት ከፍርድ ቤቱ ድሕረገጽ ማግኘት ይቻላል። ይህን የሕግ መዝገበ ቃላት ያዘጋጃችሁ ሁሉ ክብር እና ምስጋና ይገባችኋል።
ሊንክድ ኒን @Etmet Assefa

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ሕዳር 05/03/2017 ዓ.ም) የፌዴራል ጠቅላይ ፍረድ ቤት ከፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የማስማማትና የግልግል ዳኝነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደሩት የተወካዮች ምክር ቤት አባልና በሚኒስቴር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው የግልግል ዳኝነትን ፍርድ ቤት መር አድርጎ ከመዘርጋትና የወጣውን መመሪያና አሰራር አበጅቶ አደራዳሪዎች ተጠያቂነትና ሃላፊነትን እንዲሸከሙ መደረጉ መልካም ነው ያሉ ሲሆን ይህ መሆኑ ደግሞ የፍትሕ ሥርዓቱን ያጎለብታል፤ የባለ ጉዳዮች የጊዜና የገንዘብ ወጪን ይቀንሳል፤ ፍርድ ቤቶች ላይ የፋይል መጨናነቅ እንዳይኖር ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ባለጉዳዮች በራሳቸው ፍቃድ ወደዚህ ሥርዓት እንዲመጡ ማድረግ ይበጃል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ይህ መሆኑ ደግሞ ተበደልኩ ባለው ከሳሽም ሆነ በተከሳሹ ዘንድ የአሸናፊነት እና የተሸናፊነት አስተሳሰብ እንዳይኖር ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ድሪባ ፈየራ በበኩላቸው የማስማማትና የግልግል ዳኝነት በህግና መመሪያ መደገፉ ብቻ የታለመለትን ዓላማ እና ግብ ስለማያስገኝ ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ለተግባራዊነቱ መትጋት አለባቸው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ሥልጠናው የፍርድ ቤት መር አስማሚነት፣ የአስማሚዎች ሚና እና የአስማሚነት ክህሎት፣ የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሂደቶች እና የቤተሰብ አስማሚነት ተግባራዊ ተሞክሮ ዳሰሳ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰጥ ሲሆን፤ ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተወጣጡ 50 ረዳት ዳኞች የሚሳተፉበትና ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚሰጥ ሥልጠና ነው፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም) የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትሕና ሕግ ቋሚ ኮሜቴ አባላት በፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት አያት ጨፌ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት የመስክ ምልከታ ጉብኝት አደረጉ፡፡ በጉብኝታቸው የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለአገልግሎት የሚጠቀምባቸውን የስልጠና ክፍሎች፣ የቤተ መጽሃፍት፣ የኢ-ላይበራሪ፣ የመረጃ ማዕከል፣ የሰልጣኞች መኝታ ክፍልና መሰል ነገሮችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ከኢንስቲትዩቱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በዚህም የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች ተቋሙ ከተሰጠው ሃላፊነት አኳያ የሚሰራቸውን ሥራዎች በማብራራት እስካሁን ያጋጠሙ ችግሮችንና የተወሰዱ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማንሳት ለሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ አባላት አብራርተዋል፡፡ የቋሚ ኮሚቴ አበላት በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ለሕግና ፍትሕ ዘርፉ የሚሰጠው ግልጋሎት ጉልህ መሆኑን በማንሳት የፍትሕ ዘርፉ ያጋጠመውን ስብራት ለመጠገን ተቋሙ የሚሰጣቸውን ተግባርና ሃላፊነቶች በማጠናከር ፣ ገለልተኛ የሆነ ማሰልጠኛ ተቋም እንዲሆንና የሚጠበቅበትን ያህል እንዲሰራ የበኩላቸውን ሃላፊነት እንደሚወጡ የምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

ዜና

(ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የተለያዩ ጉዳዮችን መርምሮ አጸድቋል። ምክር ቤቱ በውሎው የፌደራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን፤ ዳኞችና ዐቃቢያነ ህጎች በአግባቡ ስልጠና ወስደው የፍትህ ሰርአቱ ለመዘመን እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንድሰጡ ለማስቻል እና ተቋማትን በምርምር ለመደገፍ የሚያግዝ መሆኑን ለምክር ቤቱ አስገንዝበዋል፡፡ የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፤ የህግ ኢንስቲትዩት ከስራ አስፈጻው ነፃና ገለልተኛ ሆኖ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚመራለት ቋሚ ኮሚቴ በዝርዝር ሊያየው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የፌደራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ፤ ለዝርዝር እይታ አዋጅ ቁጥር 11/2017 አድርጎ ለህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ መርቷል፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ በፕሮግራሙ መዝጊያ ላይ በመገኘት የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና በሚንስትር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው ኢንስቲትዩቱ የህግ ባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ የፍትሕና ሕግ ዘርፉ ቅሬታ የማይቀርብበት፣ የህብረተሰቡም የፍትሕ ጥያቄ የሚመለስበት እንዲሆን መሰል ስልጠናዎችን በማዘጋጀት ሃላፊነታችንን እንወጣለን ፤ ነገር ግን ሥልጠና በራሱ ደግሞ ውጤት አይደለምና ሥልጠናውን የሚያገኙ አካላት የሰለጠኑትን ሥልጠና በተግባር ማዋል አለባቸው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ይህ የአሰልጣኞች ስልጠና ደግሞ የወደፊት አሰልጣኞችን የምናፈራበትና የሃገር አደራ የምንሰጥበት የስልጠና አይነት እንደመሆኑ መጠን በዚህ ሥልጠና ላይ ለመሳተፍ እድል ያገኛችሁ ሲኒየር የህግ ባለሙያዎች በሙሉ የሰለጠናቹህትን ሥልጠና ለሌሎች በማድረስና ታናናሾቻቹህን በማብቃት ረገድ ትልቅ ሃላፊነት እንዳለባቹህ ልታውቁት ይገባል ሲሉ ሚኒስቴር ዴዔታው መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ሰልጣኞች በበኩላቸው ከአሁን በፊት የወሰዷቸው ስልጠናዎች ቢኖሩም የአሁኑ ስልጠና ግን ከእስካሁኑ የተለዬ እና ለወደፊት ሥራቸውም ግብዓት የሚሆን ሥንቅ እንደያዙበት ተናግረዋል፡፡ ይህ የአሰልጣኞች ሥልጠና የሕግ ባለሙያዎች በሚያሰለጥኑበት ወቅት እንዴት አይነት የስልጠና መንገድ መከተል እንዳለባቸው ግብዓት የሚገኙበት የስልጠና አይነት ሲሆን ከጥቅምት 19/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆዬ ነው፡፡ ሁለተኛው ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና ከህዳር 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም) የቻይናው ብሔራዊ የዳኞች ኮሌጅ (National Judges College) ከፍተኛ አመራሮች በፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት አያት ጨፌ ግቢ ውስጥ በመገኘት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አደረጉ በጉብኝቱ ላይ በሚንስትር ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ እና በሚንስትር ዴዔታ ማዕረግ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ ስለ ተቋሙ በቂ መረጃ የሰጡ ሲሆን በዚህም ኢንስቲትዩቱ የተሰጡትን ተግባርና ሃላፊነቶች ለእንግዶቹ አብራርተዋል፡፡ በዚህ ጉብኝት ኢንስቲትዩቱ በአያት ጨፌ ግቢ ውስጥ የተሟሉለት ግብዓቶችንና የጎደሉትን ነገሮች በማዘዋወር ያስጎበኟቸው ሲሆን በሁለተኛ ፌዝ ሊሰሩ የተያዙ ዕቅዶችንም ጭምር ለኮሌጁ አመራሮች አስረድተዋቸዋል፡፡ በተጨማሪም ሁለቱ ተቋማት አብረው መስራት የሚችሉበት ሁኔታ ላይ የተነጋገሩ ሲሆን በምን በምን ርዕሰ ጉዳይ አብረው ቢሰሩ ውጤታማ ሊደርጋቸው እንደሚችል በመመካከር የጋራ መግባባቶች ተይዟል፡፡ በዚህም በኢኮኖሚ ዘርፍ፣ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን (አይሲቲ) ጉዳዮች፣ በስልጠና፣ በትምሕርት ዕድል እና መሰል ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አብሮ መስራት እንደሚስፈልግ ተነጋግረዋል፡፡ በጉብኝቱ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት እና የቻይናው ብሔራዊ የዳኞች ኮሌጅ (National Judges College) የተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተው ነበር፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የአሰልጣኞች ስልጠና በአዲስ አበባ ከተማ መስጠት ጀመረ በስልጠናው ማስጀመሪያ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የዳኝነትና ፍትሕ አካላት ሥልጠና መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ ሰናይት አንዳርጌ ስለ ኢንስቲትዩቱ ተግባርና ሃላፊነት ለሰልጣኞች በማጋራት ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን የዛሬው ስልጠና በዋናነት የወደፊት አሰልጣኞችን ለማፍራት ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በዋናነት በሃገሪቱ ያሉ የሕግ ባለሙያዎችን በማብቃት ረገድ ትልቅ ሥራ ይሰራል ያሉት ወ/ሮ ሰናይት የአሰልጣኞች ሥልጠና፣ የቅድመ ሥራ ሥልጠና፣ የስራ ላይ ሥልጠና እና የሕግ አመራሮች ሥልጠና እንደሚሰጥ ጭምር አብራርተዋል፡፡ የአሰልጣኞች ስልጠና በዋናነት የአሰለጣጠን ዘዴ ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰጥ ሲሆን በዚህ ሥልጠና ላይም ከጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ ከአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ እና ከፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዪት የተወጣጡ 33 የህግ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ይህ ሥልጠና የአሰለጣጠን ፍላጎት ዳሰሳ፣ የስልጠና መንገዶች፣ ሰልጣኞችን ማበረታታትና የስልጠና ግምገማ ላይ ትኩረት በማድረግ ሰልጣኞችን እንዴት መያዝ እንዳለብን፣ እና ከስልጠናው በኋላ የምናገኘውን ውጤት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰጥ ሥልጠና ነው፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

ዜና

(ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም) 17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ በመላ ሀገሪቱ ተከብሮ እንደሚውል ይታወቃል፡፡ ይህንንም ምክንያት በማድረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ባለሙያዎች በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ አክብረውታል፡፡ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሰኞ የሚከበር ሲሆን የዘንድሮው ዕለት “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ በዛሬው ዕለት ተከብሮ ይውላል። በዚሁ መሰረት ይህ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በመላ ሃገሪቱ ያሉ የመንግስት ተቋማት፣ በመከላከያ ሠራዊት ካምፖች ፣ በኢትዮጵያ ኢምባሲዎችና ሚሲዮኖች ይከበራል።

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(መስከረም 30/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለተወጣጡ ባለሙያዎች በፍርድ ቤት ችሎት ዘገባ ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ፡፡ በስልጠናው ላይ የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ምትኩ ማዳ በንግግራቸው ዝግጅቱ አጭርና ውይይታዊ የስልጠና መርሃ ግብር መሆኑን በመጥቀስ፣ በመሆኑም ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ወደ ፊት በምናደርጋቸው የፍርድ ችሎት ዘገባዎች ላይ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡ የዕለቱ የክብር እንግዳና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በንግግራቸው መገናኛ ብዙሃን የተጣለባቸው ተግባርና ሃላፊነቶችን ከመወጣት ረገድ በአግባቡ መስራት ይጠበቅባቸዋል ያሉ ሲሆን በዚህም ማህበረሰቡ ሊያውቃቸው የሚገቡ መረጃዎችን የህዝብ አይንና ጀሮ በመሆን የፍርድ ቤት ጉዳዮችን በመዘገብ ትክክለኛ እና የተሟላ መረጃ ለህዝብ ማቅረብ፣ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሕዝቡን የሕግ ግንዛቤ ማዳበር፣ አስቀድሞ በማስተማር ወንጀል እንዳይሰራ መከላከል፣ በፍርድ ቤቶች አሰራር፣ ነጻነትና የሕግ የበላይነት ላይ ሊኖር የሚገባን እምነት ማጎልበትና በህገ መንግስቱ የተደነገጉ የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበራቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች በሙሉ በነጻነት ይሰጣሉ ማለት ሳይሆን የተለያዩ የሕግ እገዳዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የጠቀሱት አምባሳደሩ ከእነዚህም መካከል የተከራካሪዎችን የግል ህይወት ፣ የሕዝብን ሞራልና የሃገርን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ገደቦች ሊደረጉ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ይህ ስልጠና ከክልል መገናኛ ብዙሃን የተወጣጡ ባለሙያዎች፣ በአዲስ አበባ ከሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ባለሙዎችና ከተለያዩ የፍትሕ አካላት የተወጣጡ የሕግ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ስልጠና ነው፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(መስከረም 28/2017 ዓ.ም) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዐውደ ጥበባዊ የሕግ መዝገበ ቃላት (Encyclopedic Law Dictionary) ታትሞ ዛሬ ተመረቀ፡፡ የፌዴራል የፍትህና የሕግ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ እና ከጄስቲስ ፎር ኦል ፒ.ኤፍ. ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዐውደ ጥበባዊ የሕግ መዝገበ ቃላት (Encyclopedic Law Dictionary) ምረቃ ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች ምሁራን እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተመርቋል፡፡ በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፣ የዕለቱ የክብር እንግዳ እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ እና የጀስትስ ፎር ኦል ፒ.ኤፍ. ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ፓስተር ዳንኤል ገብረስላሴ የሕግ መዝገበ ቃላቱን በሚመለከት ንግግር ያደረጉ ሲሆን ይህንን ተንተርሶም የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡ ይህ የህግ መዝገበ ቃላት ከ4500 በላይ ቃላቶችን የያዘ ሲሆን ዘጠኝ የሕግ ምሁራንና ስድስት የሥነ-ልሳን ምሁራንን በማካተት የተዘጋጀ ነው፡፡ የፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት እስካሁን ከ20 በላይ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን እንዳደረገ የተናገሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በእነዚህ ጥናቶች ውስጥ የፍትሕና ሕግ አካላት ወጥና አንድ የሚደርግ የሕግ አተረጓጎም ችግር ይስተዋል እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ይህ የሕግ መዝገበ ቃላት መዘጋጀቱ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች ያሉ የፍትሕ ዘርፉ ተዋናዮች ወጥ የሆ አረዳድ እንዲኖራቸው ያግዛል ያሉት ክቡር አምባሳደር በተመሳሳይ የኦሮምኛ የሕግ መዝገበ ቃላትም በሶስትዮሽ እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አቅም በፈቀደ መልኩ ከኦሮማኛው የህግ መዝገበ ቃላት በኋላ በሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎችም ለመስራት ታቅዷል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በአማርኛው የህግ መዝገበ ቃላት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች ምስጋናቸውን በመቸር ንግግራቸውን አጠናቀዋል፡፡ በዕለቱ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች፣ ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን የዕውቅና እና የሽልማት መርሃ ግብር በማድረግ ዝግጅቱ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(መስከረም 20/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለስኬት ባንክ የሕግ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ በስልጠናው ማስጀመሪ ዕለት በመገኘት የእንኳን ደህና መጣቹህና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው ስለ ኢንስቲትዩቱ ተግባርና ሃላፊነት ለሰልጣኞች መረጃ በመስጠት የጀመሩ ሲሆን በዚህም ለፍትሕ ዘርፍ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ፣ የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያዎችን እንዲመጋገቡ መስራትና የፍትሕና ሕግ ሥርዓት የመረጃ ማዕከል ሆኖ ማገልገል ዋና ዋና ተግባሮቻችን እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ ሥልጠና በራሱ ግብ አይደለም ከዚህ ሥልጠና ተቋማችን ምን አተረፈ፣ እኔ ምን አተረፍኩ የሚለውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለስራችሁ ጥሩ ስንቅና ትጥቅ ይዛቹህ ልትመለሱ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት አቶ ዘካርያስ ስኬት ባንክ በኢትዮጵያ 32ኛ ባንክ በመሆን ስለተቋቋመ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ ባንኩ እንኳን ተቋቋመ እንጂ ተቋማችን ተቋማቹህ ነው ያሉት ሚንስቴር ዴዔታው ከዚህ በኋላ ለሚያስፈልጉ የፍትሕና ሕግ አቅም ግንባታዎችም ሆነ መሰል ርዕሰ ጉዳዮች አብረናቹህ ነን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ስልጠናው Civil procedure law, law of security device and new commercial law በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚሰጥ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ እስከ መስከረም 28/2017 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል፡፡ ይህ ስልጠና የተለያዩ ተቋማት በሚጠይቁት ጥያቄ መሰረት በወጪ መጋራት የሚሰጥ ልዩ ስልጠና ነው!

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

የፌዴራል የፍትህና የሕግ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ እና ከጄስቲስ ፎር ኦል ፒ.ኤፍ. ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዐውደ ጥበባዊ የሕግ መዝገበ ቃላት (Encyclopedic Law Dictionary) ምረቃ ማክሰኞ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ጀምሮ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎችና የፍትሕ ዘርፉ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(መስከረም 9/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም የስራ አፈጻጸምና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን ምን መምሰል እንዳለባቸው ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡ ውይይቱ ተመሳሳይነት ያላቸው የስራ ክፍሎች እንዴት አብረው መስራት እንዳለባቸውና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች ምን መምሰል እንዳለባቸው ያመላከተ ከመሆኑም ባሻገር ዳኝነት እና አጠቃላይ የፍትሕ አካላት ላይ ለሚስተዋሉ ችግሮች ፈጣንና ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን ለማድረግ ያለመ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተያዘው በጀት ዓመት ቨርቿል ስልጠናዎችን በማጠናከር በሁሉም ተቋማት ዘንድ ያሉ አቅሞችንና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን አሟጦ በመጠቀም በፍጥነትና በስፋት በሁሉም የሃገሪቱ ክፍል ያሉ የፍትሕ አካላትን ተደራሽ ማድርግ እንደሚገባ የተጠቆመ ሲሆን ለዚህም ዕቅድ መሳካት የሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚጠይቅ ተነግሯል፡፡ በተለይ በሰልጣኞች ምልመላ እና የስልጠና ጥያቄዎች ወጥነት ላይ ቅንጅት እንደሚጠይቅ የተገለጸ ሲሆን ክፍተቶችን ለይቶ ስልጠና የማመቻቸትና የፍትሕ ዘርፉ ያለበትን ችግር ለይቶ ጥናትና ምርምር በማድረግ ረገድ ኢንስቲትዩቱ ከሌሎች የፍትሕ ዘርፉ ተዋናዮች ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡ በስልጠና፣ በበጀት(ወጪ መጋራት)፣ ጥናትና ምርምር፣ በሞጁል ዝግጅትና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አብሮ መስራት እንደሚጠበቅ የተነገረ ሲሆን እነዚህና መሰል ርዕሰ ጉዳዮች በሁለቱም ተቋማት ዘንድ የጋራ መግባባት ተይዞባቸዋል፡፡ በዕለቱ የ2017 ዓ.ም የኢንስቲትዩቱ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ የቀረበ ሲሆን የ2016 ዓ.ም አፈጻጸም ደግሞ የኢንስቲትዩቱ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ተጠባባቂ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ዋቅጋር ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በውይይቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት፣ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ጳጉሜ 4/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የስራ ላይ ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ፡፡ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ዕለት በመገኘት ንግግር ያደረጉት በሚንስትር ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በንግግራቸው ተቋሙ የሚሰጣቸው ተግባርና ሃላፊነቶችን ለተሳታፊዎቹ በማስተዋወቅ የጀመሩ ሲሆን ይህ ስልጠናም የኢንስቲትዩቱ አንድ አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የፌዴራል የፍትሕና ኢንስቲትዩት በዋናነት እውቀት ላይ ሳይሆን ዋና የትኩረት አቅጣጫው ችሎታ እና ሥነ - ምግባር ላይ ነው ያሉት አምባሳደሩ እዚህ ያሉ ሰልጣኞች በመሉ እውቀትን ከዩንቨርሲቲ ይዘው የመጡ ስልሆነ እኛ ትኩረታችንን በተግባር የተደገፈ የዕለት ከዕለት ክንውኖች ላይ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ በስራ ውስጥ ሆናቹህ መማርና መሰልጠን ተገቢ ነው፣ ማንበብና እራስን ማዳበር ደግሞ ብልህነት ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በመሆኑም እዚህ ደረስኩኝ ብላቹህ መማርና ምንበብን ልታቆሙ አይገባም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋ፡፡ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚንስትር የሆኑት ክቡር አቶ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በንግግራቸው ደግሞ ሙያዊ መቀንጨር እንዳያጋጥማቹህ እድሜ ልካቹህን መማር፣ እራሳቹህን ማሳደግና ብቁ አድርጎ መገኘት ይጠይቃል በማለት የስራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን እውቀት ያለው፣ ክሂሎት ያዳበረ፣ ጽናት ያለው እና ህዝብና ሃገርን ለማገልገል የቆረጠ ባለሙ መሆን ይጠበቅባቹሃል ሲሉ በአደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡ ስልጠናው ከነሃሴ 6/2016 - ጳጉሜ 01/2016 ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን በአስራ አንድ የተለያዩ ርዕሶች ለ102 የቅድመ ስራ ሰልጣኞች ተሰጥቷል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

ላቀድነው ዕቅድ መሳካት የሁሉም ሰራተኛ ድርሻ አለውና ሁሉም ተረባርቦ ስኬት ላይ ልንደርስ ይገባል! አምባሳደር ደግፌ ቡላ (ጳጉሜ 1/2016 ዓ.ም) ላቀድነው ዕቅድ መሳካት የሁሉም ሰራተኛ ድርሻ አለውና ሁሉም ተረባርቦ ስኬት ላይ ልንደርስ ይገባል ሲሉ አምባሳደር ደግፌ ቡላ አዳማ ከተማ በተካሄደው የሰራተኞች መድረክ ላይ ተናግረዋል፡፡ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2017 በጀት አመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ዛሬ በአዳማ ከተማ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በሚኒስትር ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደግፌ ቡላ ባለፈው በጀት ዓመት የነበሩብንን ድክመቶች ለማረም እና ጥንካሬዎቻችንን ደግሞ ለማስቀጠል ከሙሉ ሰራተኛው ጋር መወያዬት አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ በአዳማ ከተማ ተገናኝተናል በማለት ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን በዚህም ያባለፈው ዓመት አፈጻጸም የተሸለ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ይህ አፈጻጸም የሁሉም ሰራተኛ እኩል ተሳትፎ የተስተዋለበት አልነበረም ያሉት አምባሳደሩ በመሆኑም የ2017 ዓ.ም ዕቅዳችንን ለማሳካት የሁሉም ሰራተኛ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በዚህ ውይይት ላይ ኢንስቲትዩቱ የነበረውን  አፈጻጸምና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ መሰረት በማድረግ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ተጠባባቂ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ዋቅጋሪ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን  በዚህም ባለፈው በጀት አመት ትላልቅ ስራዎች መሰራታቸውንና ከተበጀተልን  በጀት 97.4 ፐርሰት አፈጻጸም እንደነበረን አስታውሰዋል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ነሃሴ 30/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከፌዴራል ፍትሕ ተቋማት አመራሮችና ከክልል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት አመራሮች ጋር የጋራ የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡ የምክክር መድረኩ ላይ የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት የተወካዮች ምክር ቤት አባልና በሚኒስትር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው የዕለቱን የመወያያ ነጥቦች በማስታወስ የጀመሩ ሲሆን በዚህም የኢንስቲትዩቱ ቀጣይ ሶስት ዓመታት ፍኖተ ካርታ፣ የ2016 አፈጻጸምና የ2017 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎች በዋናነት የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱን ተግባርና ሃላፊነቶች ለተሳታፊዎች በማጋራት ንግግራቸውን የጀመሩት በሚኒስትር ማዕረግ የፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ መድረኩ ያስፈለገበትን አላማ በመጥቀስ፣ በ2016 ዓ.ም የነበሩ ድክመቶችን ላለመድገምና የታዩ ጥንካሬዎቻችንን ደግሞ ለማስቀጠል በማለም የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በ2017 በጀት ዓመት ኢንስቲትዩታችን በፍርድ ቤቶችና በአቃቤ ህጎች ላይ ትኩረት በማድረግ ስልጠናዎችን ይሰጣል ያሉት ክቡር አምባሳደሩ ነገር ግን ከእስካሁኑ ለየት የሚደርገው የሚሰጡ ስልጠናዎች መጨረሻ ላይ የመውጫ ፈተና እንደሚሰጥና ፈተናውን ያለፉት ብቻ ሰርተፊኬት እንደሚሰጣቸው በአንክሮ ተናግረዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ ለህግ አውጪው አካል ግብዓት የሚሆኑ ትላልቅ ስራዎችን እንሰራለን ያሉት ሚኒስትሩ ከዚህ ጎን ለጎን የፍትሕና ሕግ መረጃዎችን የመተንተንና የማደራጀት ስራም በትኩረት እንደሚሰራ ለተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡ በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የኢንስቲትዩታችን ቀጣይ ሶስት አመታት የሚኖረን ፍኖተ ካርታ ቀርቦ ግብዓት የማሰባሰብ ስራ የተሰራ ሲሆን መጨረሻም የኦሮሚያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩቶች የነበራቸውን የ2016 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም ለተሳታፊዎች አቅርበው ሃሳብ አስተያዬት ተሰጥቶበታል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

የፌደራል ፍትህና ህግ ኢንስቲትዩት በጎፋ ዞን ለተጎዱ ወገኖች 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ። (24/12/2016 ዓ.ም) የፌደራል ፍትህና ህግ ኢንስቲትዩት በጎፋ ዞን ፤ ገዜ ጎፋ ወረዳ ፤ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በድንገተኛ የመሬት መንሸራሸር አደጋ ለተጎዱ ወገኖች 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ። ድጋፉን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና በሚኒስቴር ዴዔታ ማዕረግ የፌደራል ፍትህና ህግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ ለጎፋ ዞን አስተዳደር አስረክበዋል።

መረጃ:- ሳውላ ኮሙኒኬሽን
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ነሃሴ 17/12/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡ የችግኝ መርሃ ግብሩ በጉለሌ እፅዋት ማዕከል ውስጥ የተደረገ ሲሆን በዚህም የኢንስቲትዩታችን ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የፌዴራል ጠቅላይ ፍረድ ቤት እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች ተገኝተው ተሳትፎ አድርገዋል፡፡ ይህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ እንደ ሃገር በአንድ ጀንበር ስድስት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ጥሪ የማድረጋቸው አንድ አካል ሲሆን ይህንንም መነሻ በማድረግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ተጠሪ ተቋሞች የተሰጠው ቦታ ላይ የአረንጓዴ አሻራ የማስቀመጥ መርሃ ግብሩ ተካሂዷል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

የፍትሕ ሚንስቴር ሚንስቴር ዴዔታ የሆኑት ዶ/ር ኤርሚያስ የማነ ብርሃን

(ነሃሴ 06/2016 ዓ.ም ) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዪት ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለጀማሪ አቃቢ ሕጎች የቅድመ ሥራ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡ በስልጠናው ማስጀመሪያ ዕለት በመገኘት የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት የፍትሕ ሚንስቴር ሚንስቴር ዴዔታ የሆኑት ዶ/ር ኤርሚያስ የማነ ብርሃን በንግግራቸው ስልጠናው ለሰልጣኞች እጅግ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ በመግለጽ ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል መንግስት የሚጥልባቸውን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የሚሰጣቸውን ተግባርና ሃላፊነቶች ለሰልጣኞቹ በማስረዳት ንግግራቸውን የጀመሩት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የተወካዮች ምክር ቤት አባል፣ የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች ቀጣይነት እዳላቸው በማብራራት ኢንስቲትዩቱ የሁሉም የፍትሕ ዘርፍ ነውና ልትጠቀሙበት ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ስልጠናው የሽብር ሕግ፣ የሳይበር፣ ሃሰተኛ መረጃዎችና የጥላቻ ንግግር ሕግ፣ የሙስና ወንጀል ሕግ፣ የታክስና ጉሙሩክ ሕግ፣ በሰው መነገድና በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር፣ የወንጀል ሕግ ሥነ-ስርዓት፣ የፍታብሄር ሕግ ሥነ-ስርዓት፣ የማስረጃ ሕግ፣ የወንጀል ምርመራ ክስ ዝግጅትና ችሎት ክርክር፣ የስራ ሥነ-ምግባርና ሴቶችና ሕጻናት ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሃያ የስራ ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡ በዚህ ስልጠና 103 ጀማሪ አቃቢ-ሕጎች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

ኢንስቲትዩት የስራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሰርካለም ቦጋለ

(ሰኔ 18/2016 ዓ.ም) ጉራማይሌና ወጥነት የጎደለው የስልጠና አተገባበር ወደ አንድ የሥልጠና ስርዓት መሰብሰብ እዳለበት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የስራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሰርካለም ቦጋለ ተናገሩ፡፡ ሥራ አስፈጻሚዋ ይህንን የተናገሩት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የፌዴራልና የክልሎች የስልጠና አተገባበር ሥርዓትን ወደ አንድ ለማምጣት ያለመ ጽሁፍ በአዳማ ከተማ እየቀረበ ባለበት ወቅት ነው፡፡ ጥናታዊ ጽሁፉ ያሳለፍናቸውን የስልጠና ሥርዓቶች በመቃኘት ለቀጣይ አገር አቀፍ የስልጠና አተገባበር ቀርጾ ለመስራት እንዲያስችል ታስቦ ‘’Base line survey of the disparities in implementation of trainings at federal and regional judicial training institutes’’ በሚል ርዕስ መዘጋጀቱን የተናገሩት ወ/ሮ ሰርካለም ያለፉ ክፍተቶቻችንን በመለዬት የቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለማመላከት ወሳኝ መድረክ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ የአንድን አገር እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥና የህግ የበላይነትን ለማስፈን የፍትሕ ዘርፉ ወሳኝ ሚና አለው ያሉት ሥራ አስፈጻሚዋ ለዚህም ስኬት ጥራቱን የጠበቀና የተናበበ የስልጠና ስርዓት ማዘጋጀት አንዱና ተቀዳሚ ተግባራችን ልናደርግ ይገባል ብለዋል፡፡ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በአዋጅ ቁጥር 1071/2010 ከተሰጡት ተግባርና ሃላፊነቶች መካከል በአንቀጽ 6(4) ላይ እንደሚያሳዬን ተቋማችን ከክልል የሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩቶች ጋር በመተባበር በሃገር አቀፍ ደረጃ ተፈጻሚነት የሚኖረው የስልጠና ካሪኩለም ያዘጋጃል እንደሚል ያስታወሱት ወ/ሮ ሰርካለም በመሆኑም በቀረበው ጽሁፍ ላይ ተሳታፊዎች ገንቢ አስተያዬት በመስጠት የተዘበራረቁና ወጥነት የጎደላቸው የስልጠና አካሄዶቻችንን ወደ አንድ የሚመጣ ሃሳብ እንዲሰጡ አስሰበዋል፡፡ የጥናታዊ ጽሁፉ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ ከሰባት የተለያዩ ተቋማት በተወጣጡ የጥናት ቡድኑ አባላት የተዘጋጀ ሲሆን መስተካከል ያለባቸውና ወደፊት ሊዳብሩ የሚገባቸው ሃሳብና አስተያዬቶች ከተሳታፊዎች ተሰጥተውበታል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(05/09/2016 ዓ.ም ) የፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በመከላከያ ሚንስቴር የፍትሕ ዋና ዳይሬክቶሬት የሕግ አማካሪና የፍታብሔር ጉዳይ ባለሙያዎች በቢሾፍቱ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡ በስልጠናው ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ሚንስቴር የመከላከያ ፍትሕ ዋና ዳይሬክቶሬት የስነ-ስርዓት ማስከበርና ማረሚያ ቤቶች ዳይሬክተር ኮሌኔል አበጀ እሸቱ የፌዴራል ፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩትን ለሚያመቻችላቸው ተደጋጋሚ ስልጠና በማመስገን ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን ይህ ስልጠናም ሰልጣኞች ስልጠናውን በወታደራዊ ዲሲፕሊን በመከታተል በስራ ቦታ ላይ የሚጋጥማቸውን ክፍተት ለመሙላት አይነተኛ መንገድ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ በፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የፍትሕ አካላት ሥልጠና ዴስክ ሃላፊ አቶ ብዙአየሁ አቦነህ ደግሞ መከላከያ የተከበረና የሕይወት መስዕዋትነትን የሚጠይቅ ዲሲፕሊን ነው፤ በዚህም ለሙያው ትልቅ አክብሮት አለኝ በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉ ሲሆን በመሆኑም ኢንስቲትዩታችን የመከላከያ አባላትን በማሰልጠኑ ኩራት ይሰማናል ብለዋል፡፡ ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን ከውል ውጭ ሃላፊነት፣ የፍታብሔር ስነ ስርዓት ሕግ እና የማስረጃ ሕግ በሚሉ ሶስት የተለያዩ ርዕሶች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ሚያዚያ 18/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕ እና የሕግ ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ። የዘጠኝ ወር ሪፖርቱን ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳንኤል ዋቅጋሪ እንዳብራሩት ኢንስቲትዩቱ ባለፈው አመት የነበሩ ክፍተቶችን እንደመነሻ በመያዝ በዚህ በጀት ዓመት ደግሞ ማስተካከል ያለብንና ማስቀጠል ያለብንን መልካም ተሞክሮዎች መነሻ በማድረግ እቅዳችንን አቅደን ወደ ስራ ገብተናል በማለት ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን የእያንዳንዱን ስራ ክፍል የዘጠኝ ወር አፈፃፀም ሪፖርት ለሰራተኞች አቅርበዋል። በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አበበ ሹመት በንግግራቸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት የነበረንን የስራ አፈጻጸም በመገምገም በቀሪ ሶስት ወራቶች መፈጸምና ማጠናቀቅ ያለብንን ጉዳዮች ለመለየትና የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀመጥ ተገናኝተናል ያሉ ሲሆን በዚህም የኢንስቲትዩቱ ሰራተኛ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የ2016 ዓ.ም አፈጻጸማችንን ከመቼውም ጊዜ በላይ የተሻለ ልናደርገው ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በአፈፃፀም ግምገማው ላይ በመገኘት ተሳታፊዎችን ያወያዩት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በንግግራቸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን በማበረታት ቀሪ ስራዎቻችንን ደግሞ በብቃትና በጥራት ለማከናወን የሁሉም ባለ ድርሻ አካላትን ከፍተኛ ርብርብ ይጠይቃል ያሉ ሲሆን በበጀት ዓመቱ በርከት ያሉ ጠንካራ ጎኖች ቢኖሩም ስራን የማንጠባጠብ፣ የቅንጅታዊ አሰራር መላላት፣ የመረጃ አያያዝና መሰል ችግሮች መስተዋላቸውን ጠቅሰው በቀሪዎቹ ሦስት ወራት ተቋሙን ውጤታማ ለማድረግ መልካም ሰብዕናን በመላበስ፣ ክህሎትን በመገንባትና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት ጥንካሬዎችን የበለጠ ማጎልበት ችግሮችን ደግሞ በማስተካከልና ውጤታማ ስራ በመስራት የተቋሙን ተልዕኮ ማሳካት ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው ሪፖርቱ አፈፃፀማችንን በሚገባ የዳሰሰ በመሆኑ ጥንካሬያችንና ድክመቶቻችንን የተገነዘብንበት ሪፖርት ነው ያሉ ሲሆን በቀጣይ ወራት ያሉብንን ድክመቶችን በማረምና በጋራ ተባብረን በመስራት የተጣለብንን ሃላፊነት ለመወጣት ጥረት እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ከዘጠኝ ወሩ ሪፖርት ባሻገር በኢንስቲትዩቱ ውስጥ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና መልካም አጋጣሚዎችን የሚዳስስ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ሚያዚያ 04/08/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዓመታዊ የፍትሕና ሕግ ጥናትና ምርምር ውጤቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የተዘጋጀ የባለ ድርሻ አካላት የውይይና የማረጋገጥ አውደ ጥናት አካሄደ፡፡ በአውደ ጥናቱ ላይ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የፍትሕና ሕግ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ምትኩ ማዳ የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉ ሲሆን መድረኩ ስኬታማ ለማድረግ የሚቻለውን ሁሉ እንደሚደርጉ በማሳሰብ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አምባሳደር ደግፌ ቡላ በንግግራቸው ኢንስቲትዩቱ ከተሰጡት አበይ ተግባራት ነካከል አንዱኛ ዋነኛው ችግር ፈቺ የፍትሕና ሕግ ጥናትና ምርምር ማድረግ እንደሆነ በመጥቀስ ባለፉት አመታትም ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡ ምንም እንኳን መንግስት በሀገራችን የፍትሕና ሕግ ዘርፍ ላይ የተለያዩ ሪፎርሞችን ቢደርግ የማህበረሰቡን የፍትሕ ጥያቄ ግን እስካሁን ማርካት አልቻልንም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በመሆኑም በተቋማችን የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮች በዋናነት የህብረተሰቡን ጥያቄ መነሻ በማድረግ የሚሰሩ ናቸው ብለዋል፡፡ ጥናትና ምርምሮች በዋናነት በሁለት መንገድ ይሰራሉ ያሉት አምባሳደሩ፣ አንድም በውስጥ አቅም በሌላ በኩል ደግሞ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በጥምረት እንደሚሰራ በመጠቆም ዛሬ የሚቀርቡት ጥናቶችም ከደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲና ከባህር ዳር ዩንቨርሲቲ ጋር በጥምረት የተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በዕለቱ በፌዴራል መንግስት ደረጃ የሙስና እና የኢኮኖሚ ወንጀሎች የፍትሕ አሰጣጥ ሁኔታ እና በፌዴራል መንግስት ደረጃ ከልክ ያለፈ ውንጀላ በሚል ርዕስ የተጠኑ ሁለት ጥናቶች በደብረ ብርሃንና በባህር ዳር ዩንቨርሲቲ አጥኙ ቡድኖች የቀረቡ ሲሆን የተለያዩ ሃሳብና አስተያዬቶችም ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(ሚያዚያ3/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለመከላከያ ሚኒስቴር መምሪያ ሃላፊዎች፣ ዳይሬክቶሬቶችና ሕግ ባለሙዎች ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ በስልጠናው ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት በመከላከያ ሚኒስቴር የወታደራዊ ፍትሕ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሌኔል አሰፋ ደበሌ በንግግራቸው የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት እንደዚህ አይነት ስልጠናዎችን እያመቻቸልን በመሆኑ እናመሰግናለን ያሉ ሲሆን ሰልጣኞች ስልጠናውን በወታደራዊ ዲሲፕሊን እንዲጨርሱ አሳስበዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው ሁሌም እንደምለው ማንኛውም የሃገሪቱ ዜጋ ቢያንስ የሁለት ዓመት የመከላከያ ስልጠና መውሰድ ነበረበት የሚል አመለካከት አለኝ ያሉ ሲሆን በዚህም የወታደራዊ ዲሲፕሊንን በማድነቅ ንግግራቸውን ቀጥለዋል፡፡ ይህ ስልጠና በህግ ማርቀቅ ላይ እደመሆኑ መጠን ሕጎች ሁሉ ሕግ ከመሆናቸው በፊት ያለው የመጀመሪ ምዕራፍ ነውና፣ ሕግ ማርቀቅ ላይ በቂ እውቀትና ክህሎት ካለን ለሃገር የሚጠቅም ለዜጋም የሚበጅ ሕግ ማውጣት እችላለን ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እዚህ ላይ የተበላሸ ሕግ ብዙ ነገሮችን ያበላሽብናል ብለዋል፡፡ በመሆኑም አዳዲስ ሕጎች፣ ነባር ሕጎችና የሚሻሸሸሉ ሕጎችን በሚገባ ማስተዋልና መለዬት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን ለዚህ ስልጠና ደግሞ መሰረታዊው ነገር የጥናትና ምርምር ዘርፍና የሕግ አርቃቂ አመራሮችና ባለሙያዎች አብረው መሰልጠናቸው እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ስልጠናው የተሳካ እንዲሆን ምኞታቸውን በመግለጽ ንግግራቸውን የቋጩት የተከበሩ አቶ ዘካሪስ የሃገር ሰላምን በማስከበር አገርን በማጽናት ትልቅ ሃላፊነት ያለበት ተቋም ጋር አብረን በመስራታችን ደስተኛ ነን፤ ወደፊትም በጋራ መስራትና መተባበር ባሉብን ጉዳዮች ሁሉ አብረናቹህ ነን ሲሉ ቃል ገብተዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(መጋቢት 27/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለደረጃ እድገት ለሚወዳደሩ ዳኞች የፅሁፍ ፈተና እየሰጠ ነው። ኢንስቲትዩቱ ከሚሠጣቸው አገልግሎቶች መካከል አንዱ የፅሁፍ ፈተና እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን የግልም ሆነ የመንግስት ተቋማት በጥያቄያቸው መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(መጋቢት 25/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ለሲቪል ሰርቪስ አዲስ የተቀጠሩ ዳኞች እና ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ባለሙዎች ልዩ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ ልዩ ስልጠናው በሁለት የተለያዩ ቦታዎች እየተሰጠ ሲሆን ሰባት በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዲስ ለተቀጠሩ ዳኞች፣ ሶስት ከድሬድዋ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የተጋበዙ ባለሙዎችና እና ለ20 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ባለሙዎያች የተመቻቸ ነው፡፡ አስሩ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሰልጣኞች ከመጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ስልጠናቸውን የጀመሩ ሲሆን የፍታብሄር ስነ-ስርዓት ሕግ፣ የማስረጃ ሕግ፣ የውሳኔ አጻጻፍ፣ የጉዳዮች ፍሰትና የችሎት አመራር፣ የዳኝነት ስነ-ምግባር፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ዝግጅትና አተገባበር በሚሉ ርዕሶች ላይ ለተከታታይ አስራ ስድስት ቀናት የሚቆዩ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ሰልጣኞች ከመጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምረው ስልጠና የገቡ ሲሆን የግልግል ዳኝነትና የእርቅ አሰራር ስርዓት አዋጅ ላይ ለተከታታይ አስር ቀናት የሚቆዩ ይሆናል፡፡ ልዩ ስልጠና ማለት በመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ጥያቄ መሰረት በመጠነኛ ክፍያ የሚሰጥ የስልጠና አይነት ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

(መጋቢት 22/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከአሶሳ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባባር ያዘጋጀው 8ኛው ሃገር አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን አገኘ፡፡ በውድድሩ ሃያ አምስት ዩንቨርሲቲዎች እንዲሳተፉ የተደረገ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አስራ ሁለት ዩንቨርሲቲዎች በተለያዩ ማጣሪዎች ተለይተው ላለፉት ሁለት ቀናት የጥሎ ማለፍ ዙሮችን ሲያካሂዱ ቆተዋል፡፡ በተደረጉ የማጣሪያ ዙሮች የድሬድዋ ዩንቨርሲቲ እና የሰላሌ ዩንቨርሲቲ ለመጨረሻ ዙር የደረሱ ሲሆን ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ ደግሞ ከፌዴራል መስሪያ ቤቶችና ከተለያዩ ዩንቨርሲቲዎች የተወጣጡ ዳኞችን በማሳተፍ የማወዳደር ስራው ሲካሄድ አርፍዷል፡፡ በዚህም የድሬዳዋ ዩንቨርሲቲ አንደኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ የሆነ ሲሆን የሰላሌ ዩንቨርሲቲ ሁለተኛ እንዲሁም የባህር ዳር ዩንቨርሲቲ ደግሞ ሶስተኛ በመውጣት የስምንተኛው ሃገር አቀፍ ምስለ ችሎት ውድድር አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡ በዕለቱ ሁለቱም የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ዘካሪስ ኤርኮላ እና አቶ ምትኩ ማዳ የተገኙ ሲሆን የስልጠና እና የፍትሕ ስርዓት ማሻሻያ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዘካሪስ ኤርኮላ የኢንስቲትዩቱ ን ተግባርና ሃላፊነት ለታዳሚው ያብራሩ ሲሆን የሕግ ትምህርት ቤቶችንም መደገፍ አንደኛው ተግባራችን እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው! ነባሩ የፌስቡክ ገጻችን በመጠለፉ ምክንያት በአዲስ የፌስቡክ ገጽ መረጃዎቻችንን ይከታተሉ!!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የሥራ አመራር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሰርካለም ቦጋለ
የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ

(መጋቢት 6/2016 ዓ.ም) የተዘበራረቁ የስልጠና ሥርዓቶችን ወደ አንድና ወጥ የሆነ አሰራር ለማምጣት የሚያግዝ የልምድ ልውውጥና የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ በዕለቱ የእንኳን ደህና መጣቹህና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የሥራ አመራር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሰርካለም ቦጋለ በንግግራቸው መንግስት ለፍትሕና ሕግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ነው ያሉ ሲሆን ኢንስቲትዩታችንም ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት የተለያዩ ሃላፊነቶችን ተቀብሎ የፌዴራልና የክልል ፍትሕና ሕግ ባለሙያዎችን ከማብቃት ረገድ እየሰራና እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል፡፡ ልክ እንደ ፌዴራሉ የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ሁሉ የተለያዩ ክልሎችም የራሳቸውን የፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ማዕከል በመክፈት የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጡ ይገኛሉ ያሉት መሪ ስራ አስፈጻሚዋ ነገር ግን በእነዚህ ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ የአሰራርና የአሰለጣጠን ልዩነቶች እየጎሉ በመሄዳቸው ልዩነቶችን ለማጥበብና አንድና ወጥ የሆነ አሰራር ለማምጣት በማለም የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ “አንድ ላይ መሰብሰብ ጅምር ነው፤ አንድነትን ጠብቆ መጓዝ እድገት ነው፤ አብሮ መስራት ደግሞ ስኬት ነው!” የሚለውን የአሜሪካዊ ጸሃፊ ኤድዋርድ ኤቨርት ጥቅስ ዋቢ በማድረግ ንግግራቸውን የቋጩት ወ/ሮ ሰርካለም እኛም ወጥ የሆነ አሰራርን በመዘርጋትና አብረን በመስራት የህዝባችንን የፍትሕ ጥያቄ ልንመልስለት ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የልምድ ልውውጥና ውይይት መድረኩ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን እስካሁን የትግራይና የኦሮሚያ የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ማሰልጠኛ ተቋሞች ተሞክሯቸውን አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ነው፡፡
መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው! ነባሩ የፌስቡክ ገጻችን በመጠለፉ ምክንያት በአዲስ የፌስቡክ ገጽ መረጃዎቻችንን ይከታተሉ!!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

የስልጠናዉ ማጠቃለያ መርሀ ግብር

(መጋቢት 02/2016 .ም) ለትግራይ ክልል የፍትሕ አካላት በተለያዩ ርዕሶች ሲሰጥ የቆየው የአራት ቀናት ስልጠና ዛሬ ፍጻሜውን አገኘ፡፡ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከአጋዚ የፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በመቀሌ ከተማ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ የትግራይ ክልል የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና የአጋዚ የፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ጸጋዬ ብርሃን፣ የትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ካህሳይ ገ/መድህን እና የአጋዚ የፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ሃላፊ አቶ ሃፍቶም አረጋዊ ለሰልጣኞቹ የሰርተፊኬት ፕሮግራምና የስራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን በዚህም የሰለጠኑትን ስልጠና በተግባር እንዲያውሉ አሳስበዋል፡፡ ስልጠናው በዋናነት የማነቃቂ ስልጠና፣ የንግድ ሕግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የለውጥ አመራር የሚሉ ርዕሶች የተዘጋጀ ሲሆን ለተከታታይ አራት ቀናት ሲሰጥ ቆይቶ ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው! ነባሩ የፌስቡክ ገጻችን በመጠለፉ ምክንያት በአዲስ የፌስቡክ ገጽ መረጃዎቻችንን ይከታተሉ!!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

ስልጠናዉ በመካሄድ ላይ

ስልጠናው ከተጀመረ ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን በዚህም በሶስት የተለያዩ ቡድኖች የተከፋፈለ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡ በዛሬው ስልጠና የክልሉ ዳኞችና አቃቤ ህጎች የንግድ ሕግ ላይ እየተወያዩ ሲሆን የአጋዚ የሕግና ፍትሕ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ሰራተኞች ደግሞ የአገልግሎት አሰጣጥና የለውጥ አመራር በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ይገኛሉ! በእነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች ላይየሚሰጠው ስልጠና የሚቀጥል ሲሆን በኘገው ዕለት ስልጠናው የሚናቀቅ ይሆናል!
መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

ሰላም፣ ፍትሕና ዲሞክራሲ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሃገራዊ ኮንፍረንስ በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በመካሄድ ላይ

(የካቲት 30/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከመቀሌ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሰላም፣ ፍትሕና ዲሞክራሲ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሃገራዊ ኮንፍረንስ በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ በሃገራዊ ኮንፍረንሱ ላይ የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት የመቀሌ ዩንቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አብዱልቀድር ከድር የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ይህንን ዕድል በማመቻቸቱ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ወቅታዊ በሆነው የሰላም፣ የፍትሕና ዲሞክራሲ አጀንዳዎች ላይ ኮንፍረሱን በማዘጋጀታችን ኩራት ተሰምቶናል ብለዋል፡፡ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና የዕለቱ የክብር እንግዳ አምባሳደር ደግፌ ቡላ በመክፈቻ ንግግራቸው ያለፈ ታሪካችን ወጣ ገባ የበዛበት፣ የሚያስደስትም የሚያሳዝንም ታሪኮች የታጨቁበት ምዕራፍ በመሆኑ መጥፎ ታሪኮቻችንን ላንደግማቸው፣ ቁስሎቻችን ልናክም፣ ወደ አንድነት ልንመጣ፤ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ፊት ልንገሰግስ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ከመቀሌ ዩንቨርሲቲ ጋር ይህንን ኮንፍረንስ ስናዘጋጅ ያለፈውን ክፉ ቀን እረስተን ወደ ተሻለ ወዳጅነት፣ አንድነትና መተባበር የሚስችለን መንገድን ምሁራን አጥንተው እንዲጠቁሙን በማሰብ ነው ያሉት አምባሳደሩ በመሆኑም በእነዚህ ጉዳዮች ላይ አዳራሽ ውስጥ ብቻ ተነጋግረን መውጣት ሳይሆን በዕለት ከዕለት ኑሯችን ውስጥ ተግባራዊ ልናደርጋቸው የሚገቡን ሁነቶች ናቸው ብለዋል፡፡ ኮንፍረንሱ ስድስት ከተለያዩ የህግ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ የዘርፉ ሙሁራን ጥናታዊ ጽሁፍ የሚያቀርቡበት ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

የመስክ ጉብኝት
ከኢንስቲትዉታችን የተበረኩ የኤሌክትሮኒክ እቃዎች ርክክብ

((የካቲት 29/06/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በውቅሮ ከተማ የሚገኘውን የአጋዚ ፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩትን ጎበኙ! ዋና ዳይሬክተሩ በጉብኝታቸው ኢንስቲትዩቱ በጦርነት ወቅት የደረሰበትን ጉዳት የተመለከቱ ሲሆን በዚህም ይበጃል የሚሉትን ምክረ ሃሳብ ለኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አመራሮች አካፍለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከኢንስቲትዩት የተለገሱ የተለያዩ የኤልክትሮኒክስ ግብዓቶችን ለአጋዚ ፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀፍቶም አረጋዊ ያስረከቡ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ በግብዓት እስኪሟላና የዕለት ከዕለት ተግባሩን እስከሚጀምር ድረስ አብረናቹህ ነን ብለዋል፡፡ የአጋዚ ፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀፍቶም አረጋዊ ለተደረገላቸውና ወደ ፊትም ለሚደረግላቸው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን የተሰጣቸው ፕሪንተርና ኮምፒውተር የተለያዩ ስራዎችን ለማስጀመር እንደሚግዛቸው ተናግረዋል፡፡ በድጋፉ አምስት ኮምፒውተር እና አምስት ፕሪንተር የተለገሰ ሲሆን ወደፊትም ተጨማሪ ግብዓቶችን የማሟላት ተግባር አብረው እንደሚፈጽሙ ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡ መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

ከዚህ በኋላ አዳዲስ መረጃዎችን በቪድዬ ከስር ባለው ሊንክ እንለቃለን! በመሆኑም ወዳጅነታችንን ለማጠናከር ገብታቹህ ፎሎ ማድረግ አትዘንጉ! እናመሰግናለን!! ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ የትግራይ ክልል ፍትሕ አካላት ሥልጠና ላይ የተናገሩት

የመስክ ጉብኝት
ከኢንስቲትዉታችን የተበረኩ የኤሌክትሮኒክ እቃዎች ርክክብ

((የካቲት 29/06/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በውቅሮ ከተማ የሚገኘውን የአጋዚ ፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩትን ጎበኙ! ዋና ዳይሬክተሩ በጉብኝታቸው ኢንስቲትዩቱ በጦርነት ወቅት የደረሰበትን ጉዳት የተመለከቱ ሲሆን በዚህም ይበጃል የሚሉትን ምክረ ሃሳብ ለኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አመራሮች አካፍለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከኢንስቲትዩት የተለገሱ የተለያዩ የኤልክትሮኒክስ ግብዓቶችን ለአጋዚ ፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀፍቶም አረጋዊ ያስረከቡ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ በግብዓት እስኪሟላና የዕለት ከዕለት ተግባሩን እስከሚጀምር ድረስ አብረናቹህ ነን ብለዋል፡፡ የአጋዚ ፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀፍቶም አረጋዊ ለተደረገላቸውና ወደ ፊትም ለሚደረግላቸው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን የተሰጣቸው ፕሪንተርና ኮምፒውተር የተለያዩ ስራዎችን ለማስጀመር እንደሚግዛቸው ተናግረዋል፡፡ በድጋፉ አምስት ኮምፒውተር እና አምስት ፕሪንተር የተለገሰ ሲሆን ወደፊትም ተጨማሪ ግብዓቶችን የማሟላት ተግባር አብረው እንደሚፈጽሙ ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡ መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ
የአጋዚ የፍሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ፀጋዬ እና ከኢንስቲትዉታችን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ

(የካቲት 29/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከአጋዚ የፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለትግራይ ክልል ፍትሕ አካላት በመቀሌ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡ በስልጠናው ላይ በመገኘት እንኳን ደኅና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንትና የአጋዚ የፍሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ፀጋዬ ብርሃነ በንግግራቸው እንደዘኢህ አይነት ስልጠናዎች ተቋርጠው እንደቆዩና ከሶስት ዓመት በላይ መጀመሩን በመግለጽ ለዚህም የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በቀጣይም እነንደዚህ አይነት ስልጠናዎችን እንደሚመቻችልን ባለሙሉ ተስፋ ነን ያሉት ዶክተር ፀጋዬ ለዚህም ሲባል የክልሉ ፍትሕ ቢሮ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱን የአጋዚ ፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ከፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ጋር በቅርበት ለመስራት ዝግጁ ናቸው ብለዋል፡፡ የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በመክፈቻ ንግግራቸው የክልሉ የፍትሕ ዘርፍ መነቃቃት ይጠበቅበታል፣ ለዚህም ሲባል ካሉን የስልጠና ዕቅዶች ቅድሚ በመስጠት ነው ወደ እናንተ የመጣነው ያሉ ሲሆን ሰልጣኞችም የነበርንበትንና ያሳለፍነው ነገር ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ ሳይሆን ወደ ፊት ማሰብባ ተራማጅ አስተሳሰብን ማካበት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ የዚህ ስልጠና ዋና አላማ የፍትሕ ዘርፉ ማብቃት ቢሆንም ስልጠና በራሱ ግብ አይደለምና የሰለጠነውን በተግባር ማዋልና በቴክኖሎጂ በመደገፍ እራሳችንን ማብቃት ይጠበቅብናል ያሉት አምባሳደሩ በመሆኑም በእጅ ስልኮቻችን ሳይቀር በመጠቀም እራሳችንን ማሳደግና ከሌሎች የተሻልን ሆነን መገኘት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ ስልጠናው የክልል ዳኞችን፣ አቃቤ ሕጎችንና የአጋዚ የፍሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞችን ያካተተ ሲሆን በዚህም የማነቃቂ ስልጠና፣ የንግድ ሕግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የለውጥ አመራር የሚሉ ርዕሶች ተካተውበት ለተከታታይ አራት ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ነው! ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et

የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ
ሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በመካሄድ ላይ

(የካቲት 25/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለሕግ ትምህርት ቤት ዲኖችና መምህራን የተዘጋጀ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡ በስልጠናው ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው ሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በዕለት ከዕለት ኑሯችን ውስጥ ጣልቃ በመግባት ተጽዕኖ የሚሳድርበት ወቅት ላይ ደርሰናል ያሉ ሲሆን በመሆኑም በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥም በሰው ሰራሽ አስተውሎቶች ምክንያት አሉታዊና አዎንታዊም ተጽዕኖዎች እየተስተናገዱ ነው ብለዋል፡፡ በተለይ ደግሞ ተማሪዎች የጥናት ጽሁፋቸውን በሚሰሩበት ጊዜ፣ አሳይመንት በሚሰጣቸው ጊዜ፣ እንዲሁም አንዳንድ ተሳትፎዎች ላይ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ጥገኛ የሚሆኑበት ሁኔታ ይስተዋል ያሉ ሲሆን በመሆኑም እነዚህን መልካም አጋጣሚዎች እንዴት ልንጠቀምባቸው ይገባል የሚለው ላይ በመወያዬት የጋራ መግባባትን ይገባል ብለዋል፡፡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት በተፈጥሮው ከባድ ስራዎችን የማቅለል፣ የስራ ጫናን ማቅለል፣ የቋንቋዎችን መደበላለቅ የመቀነስ፣ ጥናታዊ ጽሁፎችን የማገዝ፣ እራስን ለማስተማር የተለያዩ ዕድሎችን የማመቻቸቱ ፣ የጊዜና የበጀት ብክነትን መቀነሱ እና መሰል ጥቅሞች እንዳሉት የተነገረ ሲሆን ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ የግለሰቦች ሚስጢር አለመጠበቅ፣ ለመቆጣጠር አመቺ አለመሆን፣ ወንጀልን በተለይም ደግሞ የበይነ መረብ ወንጀሎች እንዲስፋፉ ማድረጉ፣ የሰዎች ቴክኖሎጂ ላይ ጥገኛ መሆንና መሰል ድርጊቶች የሰው ሰራሽ አስተውሎት ጉዳቶች እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማለት ከስሙ እንደምንረዳው ሰው ሠራሽ ክህሎት ማለት ሲሆን ይህም ሰዎች ከሚሰሩት ስራዎች ወይም ከሚተገብሩት ችሎታዎች በተቃራኒው በተለያዩ ማሽኖች ማለትም በኮምፒውተሮች በስልክ በ ሮቦቶች እንዲሁም በተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዲቫይሶች የሚተገበር ወይም ደግሞ የሚሰራ ክህሎት ነው፡፡
መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!

የፊርማ ስነ ስርአት በመካሄድ ላይ

(የካቲት 22/06/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት “ሴንተር ፎር ናሽናል ኤንድ ሪጅናል ኢንተግሬሽን ስተዲስ” ከተባለ ተቋም ጋር አብሮ ለመስራት የሚስችለውን የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱ በዋናነት በአገራዊና ጠቃሚ ጉዳዮች ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ላይ በጋራ ለሥራት፣ በፍትህና ህግ ፣በፍትህ ማሻሻያ ፣በክልላዊ እና በአገራዊ ውህደት ጉዳዮች ላይ በጥናት ላይ የተመሰረቱ ምክሮችን ለዘጋጀት፣ በምርምር ግኝቶች ላይ በመመርኮዝ ለህግ እና ለፖሊሲ ውሳኔዎች የሚረዱ ሰነዶችን ለዘጋጀት፣ እንዲሁም የፍትህ ዘርፍ ባለሙያዎችና ሠራተኞች አቅም ማሳደግና ለማጎልበት ያለመ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆን ይሆናል፡፡ ስምምነቱን የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ እና የሴንተር ፎር ናሽናል ኤንድ ሪጅናል ኢንተግሬሽን ስተዲስ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኢብራሂም ሙሉሻ የተፈራረሙ ሲሆን በተቋማቱ ያለን የሰውና ፋይናንሻል አቅርቦት በማስተባበር ለሃገር የሚጠቅም ስራ ለመስራት ያግዛል ተብሏል፡፡
መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው! ለበለጠ መረጃ፡፡-
ፌስቡክ ፔጅ፡- Federal Law and Justice Institute 2
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet

የፊርማ ስነ ስርአት በመካሄድ ላይ

(የካቲት 20/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በስልጠና እና በጥናትና ምርምር ዘርፍ መደጋገፍ የሚስችላቸውን የስምምነት ሰንድ ዛሬ ተፈራረሙ፡፡ ስምምነቱ በዋናነት የተዋረድና ጎንዮሽ የመንግስታት ግንኙነትን በተመለከተ የሚታየውን የግንዛቤና የአቅም ክፍተት ለመሙላት፣ በህገ መንግስቱ፣ ፖሊሲ፣ አዋጆችና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ላይ ሰፊ የግንዛቤና የአቅም ግባታ ስራ መስራት፣ የህግ የበላይነትና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ የባለሙ አቅም ግንባታ በማካሄድ በክልልና በፌዴራል ደረጃ ተቀራራቢ የሕጎች አተረጓጎም እዲኖር ማድረግ፣ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን በመስራት የውይይት መድረኮችን ማካሄድ ላይ ትኩረት አድረጎ ለመስራትእንዲሁም በትብብርና በቅንጅት ለመስራት የሚስችል ሲሆን የፌዴሬሽን ምር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገርና የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ ተፈራርመዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሀብት በማፈላለግ፣ ማሰባሰብና ውጤታማ አጠቃቀም ላይ ትኩረት በማድረግ ስራዎች ይሰራሉ የተባለ ሲሆን በጋራ የሚሰሩ ስራዎችን ሪፖርት ማዘጋጀት፣ ያመጡትን ለውጥ በጋራ መገምገምና የትኩረት አቅጣጫ ማስቀመጥ የስምምነቱ አንድ አካል እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ለስምምነቱ ውጤታማነት ከሁለቱም ተቋማት አንድ አንድ ፎካል ፐርሰን በመወከል ከስሩ ደግሞ ሁለት ሁለት ቴክኒካል ኮሚቴዎች የሚደራጁ ይሆናል፡፡
መረጃው፡- የሕዝብ ግንኙነቴና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ነው!

የኢትዮ ሶማሌ ላንድ የመግባቢያ ስምምነት አለም አቀፍ ህጋዊ ተቀባይነትና ያለው አንድምታ ላይ ውይይት ተካፋዮች በከፊል

የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የኢትዮ ሶማሌ ላንድ የመግባቢያ ስምምነት፣ አለም አቀፍ ህጋዊ ተቀባይነትና ያለው አንድምታ ላይ ትኩረት በማድረግ ከፍትሕ ተቋማት አመራሮች፣ ዳኞች፣ አቃቤ ህጎችና ጥሪ ከተደረገላቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡ የውይይቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በንግግራቸው በአሁኑ ሰዓት ወቅታዊና አንገብጋቢ ከሆኑ ዓብይት ጉዳዮች መካከል በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል ቀይ ባሕር ላይ ለ50 ዓመታት የሚቆይ በሊዝ ወደብን ለመጠቀም እ.ኤ.አ ጥር 01 ቀን 2024 በአዲስ አበባ የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት አንዱ አንኳር የትኩረት ነጥብ ነው ያሉ ሲሆን የስምምነቱን አለም አቀፍ ሕጋዊነትና ተቀባይነት በተመለከተ በተለያዩ አካላት ዘንድ የተለያየ ሃሳብና አለመግባባት በሰፊው እየተንጸባረቀ ይገኛል ብለዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሶስት ሃሳቦች እየተንጸባረቁ ነው ያሉት ክቡር አምባሳደር በአንድ በኩል የሶማሊያ መንግስት ስምምነቱ ሉአላዊነቷን የሚጥስ እንደሆነና ሕጋዊነት እንደሌለው በመግለጽ ጠንካራ ተቃውሞ ስታቀርብ በሌላ በኩል ሶማሊ ላንድ ነጻና ሉአላዊ እንደሆነች በማስገንዘብ ከማንኛውም አካል ጋር ስምምነት የማድረግ፣ በጋራ የመስራት መብት እንዳላት፣ የማንም ፈቃድና ይሁንታ እንደማያስፈልጋት በመጥቀስ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገው ስምምነት ሕጋዊ እንደሆነ አሳውቃለች። ሃገራችን ኢትዮጵያም በበኩሏ ስምምነቱ የማንንም አካል መብትና ጥቅም እንደማይነካና የአለም አቀፍ ህግም እንደሚደግፋት ገልጻለች። መድረኩ ከላይ የተነሱ ሶስት የተለያዩ ሃሳቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት የተዘጋጀ ሲሆን ኢትዮጵያ ከሶማሊ ላንድ ጋር ያደረገችው ስምምነት በአለም አቀፍ ደረጃና በሀገር ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ወቅታዊ የትኩረት አጀንዳ በመሆኑ ከኢንስቲትዩቱ ተግባርና ኃላፊነት አንጻር ስምምነቱን የተመለከቱ የሕግ ጉዳዮች ምን ምን እንደሆኑ መለየትና ከአለም አቀፍ ሕግ፣ መርሆዎችና ልማዳዊ አሰራሮች አንጻር ያለውን እንደምታ በተመለከተ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት እና ምሁራንን ባሳተፈ መልኩ ነፃ ውይይትና ምክክር ለማድረግ አልሞ የሃገራችንን ጥቅም ባረጋገጠ መልኩ ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀ ነው፡፡ ለመድረኩ የመወያያ መነሻ ጥናታዊ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን ሃገራችን ኢትዮጵያ ለስምምነቱ መድረስ ምክንያት ከሆኗት ነገሮች መካከል ከድህነትን ለመውጣት ያለ ጉጉትና ለመበልጸግ ካለን ፍላጎት አኳያ እንዲሁም በባህር በር የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብትን መኖር እንደ ዋና ሃሳብ ተነስተዋ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተቀመጡ አለም አቀፍ ሕጎች አንድም ፍትሕን ለማስፈን በሌላ በኩል ደግሞ ታዳጊ አገሮችን ጫና ውስጥ ለማስገባት ታልመው የተሰሩ ናቸው የሚል ሃሳብ ከተሳታፊዎች የተንጸባረቀ ሲሆን በመሆኑም ከእነዚህ ሕጎች ማነቆነት ልንወጣ ይገባለ፤ ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ስምምነቱ ከአለም አቀፍ ሕጎች ጋር የሚጣረስ እዳልሆነ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳዬት አለብን የተባለ ሲሆን በዚህም የዲፕሎማሲ ስራዎቻችን በማጠናከር አለም አቀፍ ሚድያዎችን በመጠቀም የማሳመንና ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን እንዳለብን ተጠቁሟል፡፡ መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ነው! (የፌስቡክ ፔጃችን ለጊዜው ከቁጥጥራችን ውጪ ስለሆን ማንኛውንም ሕጋዊ ያልሆነ መረጃ ተፖስቶበት ካዩ ሪፖርት በማድረግ ይተባበሩን)

የደቡብ ኢትዮጵያ የፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አባይነው አደቶ
የስልጠና ማጠናቀቂያ ሰልጣኞች ከአስልጣኛቸዉ ጋር

(የካቲት 3/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለሕግ ምርምርና ማሰልጠኛ ተቋማት አመራሮችና አሰልጣኞች በአዳማ ከተማ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ ስልጠናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት የተሰጠ ሲሆን በዚህም የማሰልጠኛ ተቋማት አመራሮች ስልጠናን በሚመለከት ሚናቸው ምን እንደሆነና ተቋማዊ የስራ ባህላችን ምን መምሰል እንዳለበት የጋራ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ተሞክሯል፡፡ በዕለቱ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ የፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አባይነው አደቶ በንግግራቸው ይህ ስልጠና የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደመሆኑ መጠን ከዚህ እንደተመለስን ስልጠናዎቻችን ምን መምሰል አለባቸው የሚለው ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር የስልጠና ስትራቴጂዎቻችንን እናስተካክላለን ያሉ ሲሆን በመሆኑም መሰልጠን ብቻውን ግብ አይደለምና የሰለጠነውን በተግባር ማዋል አለብን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በመጨረሻም የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ ጌታነህ ስለ ቨርቿል ትሬኒንግ (ስልጠና) አጭር መግለጫ የሰጡ ሲሆን በዚህም የመንግስት የወደፊት ትኩረት አቅጣጫ መሆኑን በመጥቀስ በተለይ የማሰልጠኛ ተቋማት ለስልጠናው የሚስፈልጉ ግብዓቶችን ከመለየትና ከማሟላት ረገድ ትልቅ ሃላፊነት አለባቸው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላፈዋል፡፡

ለሕግ ምርምርና ማሰልጠኛ ተቋማት አመራሮችና አሰልጣኞች ስልጠና በመካሄድ ላይ

(የካቲት 3/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለሕግ ምርምርና ማሰልጠኛ ተቋማት አመራሮችና አሰልጣኞች በአዳማ ከተማ እየሰጠ ያለው የአመራር ስልጠና ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል፡፡ ስልጠናው በትናንት ውሎው የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ላይ ትኩረት በማድረግ የተሰጠ ሲሆን ዛሬ ደግሞ በጠዋቱ ፕሮግራም በሪፍሌክሽን (በምልሰት) ተጀምሯል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ
ለሕግ ምርምርና ማሰልጠኛ ተቋማት አመራሮችና አሰልጣኞች ስልጠና በመካሄድ ላይ

(የካቲት 1/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለሕግ ምርምርና ማሰልጠኛ ተቋማት አመራሮችና አሰልጣኞች በአዳማ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡ በስልጠናው ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት በሚኒስቴር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው ይህ ስልጠና የተዘጋጀበትን ምክንያት ያብራሩ ሲሆን በዚህም የማሰልጠኛ ተቋማት አመራሮች ስልጠናን በሚመለከት ሚናቸው ምን እንደሆነና ተቋማዊ የስራ ባህላችን ምን መምሰል እንዳለበት የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ስልጠናው አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ በመድረኩ ለሰልጣኞች መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በንግግራቸው እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት በማድረግ የሚዘጋጁ ናቸው ያሉ ሲሆን በዚህ ስልጠናም ምንም እንኳን የስልጠና እና ምርምር ተቋማት አመራሮችን አንድ ማድረግ ባይቻልም ተቀራራቢ እውቀት እንዲኖራቸው ስለሚግዝ በአግባቡ በመከታተል ወደ ተግባር ልንለውጥ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚሰጥ “የአመራር ስልጠና” ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከተያዙ መደበኛ ስልጠናዎች መካከል አንዱ እንደሆነ ተነግሮናል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ
ከአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ጋር በመተባባር ሲሰጥ የቆየው የዕጩ አቃቢ ህጎች ስልጠና ማጠናቀቂያ መርሀ ግብር

(ጥር 28/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ጋር በመተባባር ሲሰጥ የቆየው የዕጩ አቃቢ ህጎች ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ዕለት በመገኘት የእንኳን ደህና መጣቹህና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በሚኒስቴር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው ኢንስቲትዩቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ለተሳታፊዎች በማብራራት፣ ከእነዚህ ተግባርና ሀላፊነቶች መካከል አንዱና ዋነኛው የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ነው ያሉ ሲሆን ይህ ስልጠናም የዚሁ ተግባርና ሃላፊነት አንድ አካል ነው ብለዋል፡፡ ስልጠና በራሱ ግብ አይደለመ፣ ያሉት ሚኒስቴር ዴዔታው በመሆኑም ሰልጣኞች የሰለጠናቹህትን ስልጠና በተግባር ላይ ማዋልና የፍትሕ ዘርፉን ማገዝ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ በዕለቱ ሰልጣኞች ወደ ስራ አለም ከመግባታቸው በፊት መያዝ ያለባቸው ቁም ነገሮችንና የስራ መመሪያ የሰጡት የአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ተክሌ በዛብህ፣ እንደ ሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ትልቅ የፍትሕ ጥማት ያለበትና ጠንኳራ የፍትሕ ተቋም መገንባት የሚስፈልግበት ወቅት በመሆኑ ስልጠናውን የወሰዳቹህ ዕጩ አቃቢ-ህጎች የተሰጣቹህን እድልና አደራ መወጣት አለባቹህ ሲሉ አሳስበዋ፡፡ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ የአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮን ለሚቀላቀሉ ዕጩ አቃቢ-ሕጎች የህይወት ተሞክሮ ልምዳቸውን ያካፈሉ ሲሆን የዛሬ ጀማሪዎች የነገ መሪዎች ትሆናላቹህና መበርታት፣ ማንበብና እራሳቹህን ማብቃት አለባቹህ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ስልጠናው ከጥር 07 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አስራ ስምንት ቀናት የተሰጠ ሲሆን ሰልጣኞች ወደ ስራ አለም ሲገቡ የሚገጥማቸውን ችግር መቅረፍ የሚያስችል እንደሆነ ተነግሯል፡፡

አቶ አበበ ሹመት የኢንስቲትዩቱ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ሀላፊ
ለፌዴራልና ለክልል የማረሚያ ቤት ፖሊሶች በስልጠና ላይ

(ጥር 27/05/2016 ዓ.ም) ለፌዴራልና ለክልል ማረሚ ቤት ፖሊሶች የሚሰጠው ሁለተኛ ዙር ስልጠና ዛሬ ጀመረ፡፡
በስልጠናው ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣቹህና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ሹመት በንግግራቸው ይህ ስልጠና የማረሚ ቤት ፖሊሶችን አቅም ለመገንባት ከሚደረጉ ስልጠናዎች መካከል አንደኛው ዙር ተጠናቆ ይሕ ሁለተኛው ዙር ነው ያሉ ሲሆን በመሆኑም ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ያገኘነውን እውቀት ለየተቋሞቻችን ማካፈልና ልምዳችንን የማስፋት ስራ መስራት አለብን ብለዋል፡፡ ስልጠናው በዋናነት የማረሚ ቤት ጥበቃ ደህንነት፣ የኢፌዴሪ ሕገ መንግስትና የአመክሮና ይቅርታ አሰጣጥ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ነው!
ከፌዴራልና ከተለያዩ ክልሎች ለተወጣጡ ባለሙያዎች ስልጠና ላይ

(ጥር 20/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከፌዴራልና ከተለያዩ ክልሎች ለተወጣጡ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ በስልጠናው ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣቹህና መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አበበ ሹመት በንግግራቸው ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለሰልጣኞቹ በማብራራት የጀመሩ ሲሆን በዚህም ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን ከማድረግ ባሸገር ስልጠና መስጠት፣ የፍትሕ ስርዓት ማሻሻያዎችን ማካሄድና የፍትሕና ሕግ መረጃ ማዕከል ሆኖ ማገልገል ዋነኛ ተግባራችን መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይህ ስልጠና ተቋማችን ከለውጡ ጋር ተያይዞ በዕቅዱ ከያዛቸው ተግባራት መካከል አንዱ ነው ያሉት አቶ አበበ በመሆኖም የሚሰጡ የስልጠና ርዕሶችም ዝም ብለው የተመረጡና እኛ ያስቀመጥንላቹህ ሳይሆን በተወካዮቻቹህ በኩል የስልጠና ፍላጎት በማሰባሰብ የተዘጋጁ ናቸው፤ በመሆኑም ስልጠና በባህሪው ግብ አይደለምና ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል በምትሄዱበት ተቋም ሌሎችን በማብቃት፣ የሰለጠናቹህትን በማካፈል ሃላፊነታቹህን በአግባቡ እንድትወጡ አደራ ማለት እወዳለሁ ብለዋል፡፡
ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን የታራሚዎች ሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ የማረሚ ፖሊስ ሙያዊ ሥነ-ምግባር እና ታራሚዎችን ማረምና ማነጽ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ነው!
ለአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ጀማሪ አቃቢ ሕጎች ስልጠና

(ጥር 7/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ጀማሪ አቃቢ ሕጎች የቅድመ ስራ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ በስልጠናው መክፈቻ ላይ በመገኘት ንግግር ያደሩት ዩፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ምትኩ ማዳ የአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ዐቃቢያነ ሕግ በተለያዩ ሕጎችና የአሰራር ስርዓቶች ላይ የሚሰጥ አጭር የስልጠና ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ስለመጣቹህ ከልብ አመሰግናለሁ በማለት ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ የሚሰጣቸውን ዝርዝር ተግባራትን ለሰልጣኞቹ በማብራራት ይህ ስልጠና አዲስ ለተቀጠሩ የአዲስ አበባ ዐቃቢ ሕጎች ስራ ከመጀመራቸው በፊት ስለሚሰሩበት ተቋም አሰራርና ዋና ዋና የህግ ማዕቀፎችን እንዲላመዱና እንዲውቁ የሚያግዝ የቅድመ ስራ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡
በኢንስቲትዩታችን የሚሰጡ ስልጠናዎች ዋና ግብ የፍትሕና ሕግ ስርዓቱን ብቁና ዘመናዊ ለማድረግ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና የፍትሕ አካላትን ዘመናዊ፣ ተደራሽ፣ ቀልጣፋና ውጠየታማ በማድረግ በፍትሕ ስርዓቱ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የፍትሕ ዘርፉን ማገዝ ነው ያሉት አቶ ምትኩ ዛሬ የተጀመረውም ስልጠናም የአዲስ አበባን የፍትሕ ቢሮ አቅም በተወሰነ ደረጃ በመገንባት ችግር ሊፈታ ይችላል ብለዋል፡፡ ይህ ስልጠና ኢንስቲትዩቱ ካሉበት የስራ መደራረቦች ቅድሚ በመስጠት የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ምትኩ ይህም በአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮና የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ለበለጠ እደሚጠናክር እናምናለን ብለዋ፡፡
የአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ምክትል ሓላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ በንግግራቸው ስልጠናው ብዙ ጊዜ፣ ሃብትና ጉልበት እንደወጣበት የገለጹ ሲሆን ይህንንም ታሳቢ በማድረግ ሰልጣኞች በአግባቡ ስልጠናውን በመከታተል ለተግባራዊነቱ መትጋት አለባቸው ብለዋል፡፡
ይህ ስልጠና ሰልጣኞች ወደ ስራ ሲገቡ መሬት ላይ ያለውን ሃቅ አውቀው እንዲገቡ ያግዛቸዋል ያሉት ምክትል ቢሮ ሃላፊው ኢንስቲትዩቱ ይህንን እድል በማመቻቸቱም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ስልጠናው የአዲስ አበባ ቻርተር 361/1995፣ የአዲስ አበባ የተሸሻለው የአስፈጻሚ አካላት አዋጅ 84/216፣ የፌዴራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ሕግ፣ የመሬት ሕግ፣ ሕግ ማርቀቅ፣ የአስተዳደር ውል፣ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ 234፣ የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ፣ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ፣ የፍታብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ፣ የክስ አመሰራረትና የክርክር ሂደት፣ የአቃቢ ሕጎች ስነ ምግባርና መተዳደሪ ደንብ እና የአገልግሎት አሰጣጥና ተግባቦት በሚሉ ርዕሶች ለ18 የስራ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን 45 ጀማሪ ዓቃቤ ሕጎች የሚሳተፉበት ይሆናል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ነው!

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መምሪያ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ
ዜና

(ጥቅምት 4/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ለፌዴራል ፖሊስ ህግ ባለሙያዎች፣ መርማሪዎችና የወንጀል ክትትል ባለሙያዎች በተመረጡ የሕግ ርዕሶች ላይ ስልጠና እየሰጠ ነው ፡፡ በስልጠናው ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው ሰላምን ከሚጸና፣ ወንጀልን ከሚጸየፍ፣ ህግን ከሚስከብርና ሃገርን ከሚስጠብቅ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመስራታችን ደስተኞች ነን ያሉ ሲሆን ወደፊት መሰል ስልጠናዎችም እንደሚመቻቹ ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መምሪያ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ለሰጠው የስልጠና እድል በማመስገን ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ወንጀል እየጨመረ የእኛም ቁጥር እየጨመረ ነው እንደመሆኑ መጠን ብዛት ያለው የሰው ሃይላችን ደግሞ የተራቀቁ ወንጀሎችን በፍጥነት መርምሮ ወንጀለኞችን ለፍርድ ከማቅረብ አኳያ ስልጠና አስፈላጊ ነው ብለዋ፡፡ ይህን እድል ያገኛቹህ ሰልጣች ወደ ክፍላቹህ ስትሄዱ የሰለጠናቹህትን በማካፈልና የስልጠናውን ሰነድ ሳታንጠባጥቡ በአግባቡ ሰንዶ በመያዝ ወደ ታች በማድረስ ረገድ ትልቅ ሃላፊነት ይጠበቅባቹሃል ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ በመሆኑም ስልጠናውን ፖሊሳዊ ዲሲፕሊን በተከተለ አግባብ ተከታትላቹህ እንድታጠናቅቁ አሳስባለሁ ብለዋል፡፡ ስልጠናው የፍትሃ-ብሄር ስነ-ስርዓት ህግ፣ የወንጀል ስነ-ስርዓት ህግና የሳይበር ወንጀል በሚሉ ርዕሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን ከትናንት ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡ መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ነው!

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት

(ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ከፌዴራልና ከክልል የሕግና ፍትሕ አካላት ጋር ሃገር አቀፍ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡ በመድረኩ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በንግግራቸው ኢንስቲትዩቱ ባለፈው ዓመት የሰራቸው ስራዎች፣ ያጠናቸው ጥናቶች፣ የሰጣቸው ፈታዎችና መሰል የተቋሙ ስራዎችን ለተሳታፊዎች በመጥቀስ ምንም እንኳን ኢንስቲትዩቱ ከፌዴራልና ከክልል የተወጣጡ የፍትሕ አካላትን በማሰልጠን የተሰራው ስራ መጠነ ሰፊ ነበር ያሉ ሲሆን እንደዚም ሆኖ ግን እስካሁን የሰጠናቸው ስልጠናዎች ችግር ፈቺ ሆነው የማህበረሰቡን የፍትሕ ፍላጎት መቅረፍ አልቻልንም ብለዋል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት ደግሞ እዚህ ያለን አካላት በዋናነት የፍትሕና ህግ ማሰልጠኛ ተቋማት የትኩረት አቅጣጫቸው ምን ሊሆን እንደሚገባ መነጋገርና አቅጣጫ ማስቀመጥ አለብን ያሉ ሲሆን ይህንን ማድረጋችን ደግሞ በፍትሕ ዘርፉ ላይ ያለውን ክፍተት ለመድፈንና ችግሮቻችንን ነቅሶ ለማውጣት ያግዘናል ብለዋ፡፡ በምክክር መድረኩ የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት የስልጠና ውጤት ዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ለውይይት የተከፈተ ሲሆን በዚህም ላይ የፍትሕ ዘርፉ አመራሮች ሃሳብና አስተያዬታቸውን እየሰጡ ነው፡፡ መድረኩ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዋና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ፣ የኦሮሚያና የቤንሻጉል ጉምዝ ክልሎች ፍትሕና ሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩቶች የ2015 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸምና የ2016 ዓ.ም ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ነው!
ክቡር አቶ ዘካሪስ ኤርኮላ

(ጥቅምት 26/2015 ዓ.ም) በስልጠናው ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ፍርድ ቤቶች ዋና ዳይሬክተር ኮረኔል አደም ስዑድ ለተደረገላቸው የስልጠና ዕድል በማመስገን ሰልጣኖችን እንኳን ደህና መጣቹህ ብለዋቸዋ፡፡
በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት የፍትሕ ማሻሻልና የስልጠና ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዘካሪስ ኤርኮላ በንግግራቸው ኢንስቲትዩቱ የሚሰጣቸው ዋና ዋና ተግባራትን ለተሳታፊዎች በማሳየት የሃገር አለኝታ የሆነው መከላከያ ሰራዊታችን ጋር በመስራታችን ደስተኞች ነን ብለዋል፡፡
የዛሬው ስልጠና ልዩ የሚያደርገው አሰልጣኖቻችን ሰርቲፋይ አሰልጣኝ በሆኑበት ወቅት የሚሰጥ ስልጠና መሆኑና ስልጠናው ደግሞ ለሃገር መከላከያ ሰራዊት በመሆኑ ነው ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ ስልጠና የወንጅል ህግ፣ የማስረጃ ህግና የወንጀል ስነ-ስርዓት ህግ የትኩረት አቅጣጫዎቻችን ናቸው ብለዋ፡፡ በተጨማሪም የመከላከያ ሰራዊታችን በስልጠና ዲሲፕሊን የማይታማ ነው ያሉት አቶ ዘካሪስ በመሆኑም ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ወደየችሎታችን ስንመለስ በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ ስልጠናው አያት ጨፌ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ማሰልጠኛ ተቋም እየተሰጠ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ነው!

ሰልጣኞች የግሩፕ ስራ በማቅረብ ላይ
ዜና

(ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከተለያዩ የሕግ ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ የህግ መምህራን እየሰጠ ያለው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስልጠና ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡ ስልጠናው ትናንት ጀምሮ እየተሰጠ ሲሆን የቡድን ውይይትና የኮርስ አውትላይን ገለጻ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የስልጠናው ይዘት በአስር ዋና ዋና ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን ይህም የተሳታፊዎችን አቅም ለመገንባት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ትናንት በነበረው የስልጠና ውሎ ይዘቱ አዲስ ካሪኩለም እንደመሆኑ መጠን ተሳታፊዎች ላይ ክፍተት እንደነበረ መስተዋሉን ተነግሯል፡፡ ሰልጣኞች በውሏቸው የምዕራፍ አንድ ኮርስ አውትላይንን በአምስት ቡድን በመከፋፈል እንዲወያዩና ለተሳታፊዎች እንዲያቀርቡ የተደረገ ሲሆን የሰልጣኞች ንቁ ተሳትፎ ዛሬም እንደቀጠለ መሆኑን በቦታው ተገኝተን ታዝበናል! መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ነው!

ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ

(ጥቅምት 9/2016 ዓ.ም) ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያ አዲሱ የኢንስቲትዩቱ መዋቅር የተሰራበት የአፈጻጸም ሂደት ትናንት ለሰራተኞች ቀረቦ ውይይት ተደረገበት፡፡ በዕለቱ ኢዲሱ መዋቅር ምን እንደሚመስል፣ በመዋቅሩ የሰው ሃየል የተሟሉና ያልተሟሉ የስራ ክፍሎች የትኞቹ እንደሆኑ፣ እንዲሁም የድልድል አፈጻጸሙ ምን ይመስል ነበር በሚል የተዘጋጁ ሶስት ሰነዶች በሃላፊዎች የቀረቡ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎች ከሰራተኞች ተሰንዝረው በመካከለኛና ከፍተኛ አመራሩ ምላሽ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰራተኛው በተለይም መዋቅራዊ ድልድል ያገኘው ሰራተኛ ብቃት ሊኖረውና የአገልግሎት ስርዓቱን ሊያዘምን እንደሚገባ፣ በዚህም የኢንስቲትዩቱን የአገልግሎት እርካታ በመጨመር ተገልጋዮቻችንን ልናስደስትና በፈገግታ ልናስተናግዳቸው እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ነው!

የስራ አስፈጻሚ ክፍሎች

ዜናዎች