አቶ ጌታቸው መንግስቴ:- አስተዳደራዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ

የኢንስቲትዩቱን የ3 ዓመት(2018-2020) ፍኖተ ካርታ በሚመለከት በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡

የኢንስቲትዩቱን የ3 ዓመት(2018-2020) ፍኖተ ካርታ በሚመለከት በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡

Raeesh
አቶ ጌታቸው መንግስቴ

አስተዳደራዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

የኢንስቲትዩቱን የ3 ዓመት(2018-2020) ፍኖተ ካርታ በሚመለከት በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው መንግስቴ የሁኔታ ትንተናና መነሻ ሀሳቦች፣ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫና ግቦች እንዲሁም የትግበራ፣ክትትልና ግምገማ ማዕቀፍ ላይ ሰፋ ያለ ገለፃ ተደርጎ የተለያዩ ሀገራት ልምድና ተሞክሮዎችን በማቅረብ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ከሰራተኞችና ኃላፊዎች ሀሳቦችና አስተያየቶች ተሰጥተውበት ከመድረኩ በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡

በ2016 ዓ.ም በጀት አመት የተቋማችን አመታዊ እቅድ ከእስትራቴጂክ እቅዱ ላይ በመርኮዝ በተቋሙ የሚገኙ መሪ ስራ አስፈጻሚዎችን እና የዳይሬክተር ጽ/ቤት በማስተባበር የተቋማዊ ለዉጥ ሥራ አስፈጻሚ አማካኝነት ተዘጋጅቶል፡፡ በክፍላቸን የሚገኘዉ የብቃትና የሰዉ ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ በዚህ በጀት አመት በተቋሙ አዲስ መዋቅርን መሰረት በማድረግ በብቁ የሰዉ ሀብት እንዲደራጅ ለማድረግ እቅድ በመያዝ ተፈጻሚ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም የሰዉ ሀብት ልማት ላይ በ2016 ዓ.ም እቅድ በመያዝ የተቋሙን ባለሞያዎች ለማብቃት የተለያዩ ዉጤትን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች በማቀድ እያስፈጸመ ይገኛል፡፡
የስትራቴጂክ ነክ ጉዳዩች ሥራ አስፈጻሚ የተቋሙን የአስር አመት እስትራቴጂክ እቅድ በመመርኮዝ የአጭርና የረጅም ግዜ እቅዶችን መማዘጋጀት እንዲሁም የእያንዳንዱን የስራ ክፍል በጥልቀት በማጥናት እየሰራ ይገኛል፡፡የመሰረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ በ2016 ዓ.ም የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል መልኩ በማቀድ ስራዉን እየተገበረ ይገኛል፡፡ የኢንፎርሜሽን ኮምንኬሽን ቴክኖሎጂ ስራ አስፈጻሚ በ2016 ዓ.ም የበጀት አመት በተቋሙ የተተገበሩ የቴክኖሎጂ ዉጤቶችን ባማከለ ሁኔታ በማቀድ ጀምሯል፡፡ በተጨማሪም አዲስ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ለመዘርጋት እንዲሁም ከአጋር ተቋማት ጋር በማበር የሚተገበሩ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ላይ እየሰራ ይገኛል፡፡