ክቡር አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ ምክትል ዋና ዳይሬክተር:- የሥልጠና እና የፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ዘርፍ ዋና ስራ አስፈጻሚ

ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩቨርሲቲና ከጀስትስ ፎር ኦል ጋር የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የህግ መዝገበ ቃላት ለማዘጋጀት የሶስትዮሽ ፊርማ ስምምነት ሰነድ

ከፌዴራልና ከክልል የሕግና ፍትሕ አካላት ጋር ሃገር አቀፍ የምክክር መድረክ

ከአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ጋር በመተባባር ሲሰጥ የቆየው የዕጩ አቃቢ ህጎች ስልጠና ማጠናቀቂያ መርሀ ግብር ጥር 28/2016 ዓ.ም

Raeesh
የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ

የፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይ/ር (ሚኒስቴር ዴኤታ)
የሥልጠና እና የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ዘርፍ

የሥልጠናና የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ዘርፍ በዉስጡ ሶስት መሪ ሥራ አስፈጻሚዎችን የያዘ ሲሆን እነርሱም የዳኝነትና የፍትሕ አካላት ሥልጠና መሪ ሥራ አስፈጻሚ፣ የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያና የሕግ መረጃ ማዕከል መሪ ሥራ አስፈፃሚ እና የህግ ባለሙያዎች ምዘናና ብቃት ማረጋገጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ ናቸዉ፡፡

የዳኝነትና የፍትሕ አካላት ሥልጠና መሪ ሥራ አስፈጻሚ የሚሰራቸው ዋና ዋና ሥራዎች ወደ ፍትሕ ሥርዓቱ ለሚቀላቀሉ አዲስ የሕግ ባለሙያዎች በአመለካከት፣ በክህሎት፣ በዕውቀት፣ በሥነ-ምግባር ታንጸው ወደ ሥራ እንዲገቡ ለማድረግ ሥልጠና ይሰጣል፡፡ እንዲሁም በሥራ ላይ ያሉ የፍትሕ አካላት ባለሙያዎችን የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማድረግ ችግር ፈቺ የሥራ ላይ ሥልጠና ይሰጣል፡፡ ሌላው የወጪ መሸፈኛ ክፍያ በማስከፈል በየሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የሚገኙ የሕግ ዳይሬክቶሬቶች እና ነገረፈጆች ስልጠና ይሰጣል፡፡ አሁን በአገር ደረጃ በተወሰኑ ክልሎች ብቻ የፍትህ አካት ስልጠና ማዕከል ያላቸው በመሆኑ የስልጠና ማዕከል ለሌላቸው ክልሎች ዳኞች እና ዐቃቤ ሕጎች፣ መርማሪ ፖሊሶች እንዲሁም በማረሚያ ኮሚሽን ከሰብአዊ መብት አያያዝ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሥራ ለሚሰሩ የፖሊስ አባላት የፍላጎት ዳሰሳን መሠረት ያደረገ ሥልጠና ይሰጣል፡፡ ሌላው የክልል ሥልጠና ማዕከላት ወጥ የሆነ የካሪኩሌም እና የአሰለጣጠን ሥርዓት እንዲኖራቸው ለማድረግ አግባብ ያላቸውን አካላትን በማስተባበር እና የማቀናጀት ካሪኩሌም ያዘጋጃል፣ የመስጠት የዚህ ክፍል ቁልፍ ተግባር ነዉ፡፡

የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያና የሕግ መረጃ ማዕከል መሪ ሥራ አስፈፃሚ ክፍል ዋነኛ ዓላማ የፍትህ አካላት እና የህግ ትምህርት ማሻሻያ ፕሮግራሞችን የማስተባበርና የማቀናጀት፣ የፍትህና የህግ መረጃዎችን በማሰራጨት የፍትህና የህግ ስርአቱን ለማሻሻል የሚያደርጉትን ጥረት መደገፍ ነዉ፡፡ በተጨማሪም የፍትህና ሕግ ነክ መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ በማደራጀትና በመተንተን በዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለተገልጋይ /ባለድርሻ አካላት በስፋት እንዲደርሱ ማስቻል ነዉ፡፡

የህግ ባለሙያዎች ምዘናና ብቃት ማረጋገጥ መሪ ሥራ አስፈጻሚ በተለያዩ በህግ ትምህርት ቤቶች እና በፍትህ አካላት ሥልጠና ማዕከላት የሚሰማሩ የህግ ባለሙያዎች ተገቢዉን እዉቀትና ክህሎት ያላቸዉ መሆኑን የሚረጋገጥበት የምዘና ስርዓት በመዘርጋት ተግባራዊ ማድረግ ነዉ፡፡

የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ እና ሥልጠና ዘርፍ ተጠሪ የሆኑ መሪ ስራ አስፈጻሚ ክፍሎች

የዳኝነትና የፍትሕ አካላት ሥልጠና መሪ ሥራ አስፈጻሚ

በአዳማ ከተማ ሲሰጥ የነበረውን የአሰልጣኞች ስልጠና

ለጤና ሚኒስቴር የሕግ ባለሙያዎች ልዩ ስልጠና

ለጤና ሚኒስቴር የሕግ ባለሙያዎች ልዩ ስልጠና

የሕግ ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ የህግ መምህራን ሲሰጥ የነበረው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስልጠና

ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ፍርድ ቤቶች

ከአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ጋር በመተባባር ሲሰጥ የቆየው የዕጩ አቃቢ ህጎች ስልጠና ማጠናቀቂያ መርሀ ግብር ጥር 28/2016 ዓ.ም

የዳኝነትና የፍትሕ አካላት ሥልጠና መሪ ሥራ አስፈጻሚ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናዉናል፤

  1. የኢንስቲዩቱን የሥልጠና አገልግሎት አሰጣጥ የሚያቀላጥፉ የአፈጻጸም መመሪያዎችና ማንዋሎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል እንዲሁም አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ተገቢው ማሻሻያ በወቅቱ እንዲደረግ ያደርጋል፤

  1. ከክልል የሕግ ምርምር እና ስልጠና ማዕከላት ጋር በመተባበር በአገር አቀፍ ደረጃ ተፈጻሚነት የሚኖረው የስልጠና ካሪኩለም እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል ማሻሻያዎች ሲኖሩ በካሪኩለሙ እንዲካተት ያደርጋል፤
  2. የፍትህ ሥርአቱን የሚያገለግሉ የቅድመ ሥራ ሰልጣኞችን፤ በሥራ ላይ ያሉትን ዳኖች፣ አቃቢያነ ህጎች፣ ተከላካይ ጠበቆች፣ የማረሚያ እና የመርማሪ ፖሊሶች፣ እና ሌሎች የፍትህ አካላቱ ባለሞያዎችን የአፈጻጸም ክፍተትና የስልጠና ፍላጎት እንዲጠና ያደርጋል፡፡ በጥናት ውጤቱ መሰረት ያሉትን ክፍተቶች ለመሙላት የሚያስችሉ የስልጠና ሞጁሎችና የማሰልጠኛ ጽሁፎች እንዲቀረጹና እንዲገመገሙ ያደርጋል፤ በሚሰጥ ግብአት መሰረት እንዲስተካከሉ ያደርጋል፤ መፈጸሙንም ያረጋግጣል፤
  3. Raeesh

    ወ/ሮ ሰናይት እንዳርጌ
    የዳኝነትና የፍትሕ አካላት ሥልጠና መሪ ሥራ አስፈጻሚ
    ስልክ፡-
    ሞባይል፡-251-0913617820
    ኢሜል፡-senait6178@gmail.com

    1. ለኢንስቲትዩቱ እና ለሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ከዓላማው ጋር ግንኙነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ የሕግ ማማከር አግልግሎት ይሠጣል፤
    2. ሙያዊ ብቃት እና ሥነ-ምግባርን ለማሳደግ ቀጣይነት እና ተከታይነት ያለው የስልጠና ፕሮግራም ያዘጋጃል፤ የስልጠና ተሳታፊዎችን ይለያል፣ ጥሪ እንዲተላለፍ ያደርጋል፤

    1. የፍትህ አካላትን ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እውቀት እና ክህሎት ለማዳበር የሚረዱ የስልጠና እቅዶችን ይነድፋል፣ ያስተባብራል፣ ተፈጻሚነታቸውን ይከታተላል፤
    2. የክልል የፍትህ አካላት ባለሞያዎች ማሰልጠኛ ማእከላት አሰልጣኞችን እና የህግ መምህራን አቅም ለማሳደግ የሚረዱ የስልጠና እቅዶችን ይነድፋል፣ ያስተባብራል፣ ተፈጻሚነታቸውን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፤

  1. የፌደራል የግል ጠበቆችን በጠበቆች ፍቃድ አሰጣጥ አዋጅ መሰረት ዓመታዊ የስልጠና ዕቅድ ውስጥ በማካተት፤ ስልጠናው እንዲሰጥ ያደርጋል፤
  2. በግልም ሆነ በመንግስታዊ ድርጅቶች የሚቀርቡ የስልጠና እና የፈተና አገልግሎትን በወጪ መሸፈን መመሪያ መሰረት ክፍያ ሲፈፅሙ እንዲከናወን ያደርጋል፤
  3. ወቅቱንና ደረጃውን የጠበቀ የስልጠና ስርዓተ ትምህርት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ወቅቱን ጠብቆ እንዲሻሻል ያደርጋል፤
  4. የሌሎች መሰል ሃገራዊ፤ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ተቋማትን የስልጠና አሰራርና ልምድ በመውሰድ የተሻሉ ልምዶችን በመቅሰም በስራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤
  5. ከፌደራልና ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ጉባኤ የውይይት መድረክ ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በመተባበር እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣አፈጻጸሙንም ይከታተላል፡፡
በግልም ሆነ በመንግስታዊ ድርጅቶች የሚቀርቡ የስልጠና እና የመፈተን አገልግሎትን በተመጣጣኝ ክፍያ እንዲከናወን ያደርጋል፡፡ ከዚህ ቀደም በሰጠናቸዉ ስልጠናዎች በይዘታቸዉ በአቀራረቡ እንዲሁም ጥራቱን የጠበቀ መስተንግዶዋችን ከሌሎች ተመራጭ ያደርገናል፡፡ከምንሰጣቸዉ ስልጠናዎች በጥቂቱ፡-


ለበለጠ መረጃ ያግኙን!
ወ/ሮ ሰናይት እንዳርጌ ፡- የዳኝነትና የፍትሕ አካላት ሥልጠና መሪ ሥራ አስፈጻሚ
ስልክ፡- ሞባይል፡-+251-0913617820
ኢሜል፡-senait6178@gmail.com

የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያና የሕግ መረጃ ማዕከል መሪ ሥራ አስፈፃሚ

በአዳማ ከተማ ሲሰጥ የነበረውን የአሰልጣኞች ስልጠና

ለጤና ሚኒስቴር የሕግ ባለሙያዎች ልዩ ስልጠና

ለጤና ሚኒስቴር የሕግ ባለሙያዎች ልዩ ስልጠና

የሕግ ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ የህግ መምህራን ሲሰጥ የነበረው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስልጠና

ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ፍርድ ቤቶች

በስልጠና እና ፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ዘርፍ የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያና የሕግ መረጃ ማዕከል መሪ ሥራ አስፈፃሚ የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ እና ሥልጠና ዘርፍ ሆኖ የሚያከናውኗቸው ዋና ዋና ተግባራት ፣

  1. በፍትሕ ሥርዓት ዘርፉ የሚከናወኑ የማሻሻያ ፕሮግራሞች አፈጻጸም ይከታተላል፤
  2. የፍትሕ ሥርዓት የማሻሻያ ፕሮግራሙን አፈጻጻም በሚመለከት ለሚመለከታቸው የፍትሕ አካላት ግብረ መልስ ይሰጣል፤
  1. የፍትሕ ሥርዓት ዘርፍ መልካም ልምዶችና ተሞክሮዎች የሚቀመሩበትንና የሚስፋፉበትን ስርአት መዘርጋት እና ነፃ፣ ገለልተኛ፣ ብቁና ውጤታማ የፍትሕ ሥርዓት ይገነባል፤
  2. የፍትሕ አካላት አሰራራቸውን ለማሻሻል ለሚያደርጉት የስራ እንቅስቃሴ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤
  3. የፍትሕ አካላትን ዘመናዊ፣ ተደራሽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ በፍትሕ ሥርዓቱ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ይሰራል፤
  4. የፍትሕ ተቋማት የጋራ መድረክ ስራዎችን ያስተባብራል፤
  5. የፍትሕ ሥርዓትና እና የሕግ ትምህርት ማሻሻያ ስራዎችን የሚመለከቱ አዳዲስ ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን ይቀርጻል፤

Raeesh

አቶ አረጋ ሱፋ፡-
የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያና የሕግ መረጃ ማዕከል መሪ ሥራ አስፈፃሚ
ስልክ፡-
ሞባይል፡-+251-0944090103
ኢሜል፡-aregasufa2022@gmail.com

  1. የሕግ ትምህርት ቤቶችን በቁሳቁስ ይደግፋል፣ ለሕግ መምህራንና አመራሮችን በማስተማር ሥነ-ዘዴ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ይሰጣል፤
  2. በአገር አቀፍ ደረጃ ተፈጻሚነት የሚኖረው የሕግ ትምህርት ካሪኩለም ቀረጻና ክለሳ ሰራዎችን ያስተባብራል፤
  3. አገር አቀፍ የተቀናጀ የፍትሕና ሕግ መረጃ ስርአት እንዲዘረጋ በማድረግ የፍትሕና የሕግ መረጃ ማዕከል ያደራጃል፤
  1. የአገርቱን የፍትሕ ሥርዓት ትክክለኛና የተሟላ ገፅታ የሚያሳይ መረጃ የመሰብሰብ፣ የማደራጀትና የመተንተን ሥራ ይሰራል፤
  2. የፍትሕ አካላት ነፃ፣ ገለልተኛ፣ ብቁ ሆኖ ውጤታማ ሥራ እንዲያከናውኑ የፍትሕና ሕግ ነክ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ ተገልጋዮችን/ ባለድርሻ አካላትን ለማርካት ይሰራል፤


ለበለጠ መረጃ ያግኙን!
አቶ አረጋ ሱፋ :- የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያና የሕግ መረጃ ማዕከል መሪ ሥራ አስፈፃሚ
ስልክ፡- ሞባይል፡-+251-0944090103
ኢሜል፡-aregasufa2022@gmail.com

የህግ ባለሙያዎች ምዘናና ብቃት ማረጋገጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ

የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት የህግ አሰልጣኞች የምዘና አተገባበር ወርክ ሾፕ ህዳር 2015 ዓ.ም የመክፈቻ ፕሮገራም

የህግ አሰልጣኞች የምዘና አተገባበር ወርክ ሾፕ በመካሄድ ላይ ህዳር 2015 ዓ.ም

የህግ አሰልጣኞች የምዘና አተገባበር ወርክ ሾፕ በመካሄድ ላይ ህዳር 2015 ዓ.ም

የህግ ባለሙያዎች ምዘናና ብቃት ማረጋገጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት፡-

  1. የህግ መምህራንን እና በፌዴራል እና በየክልላት የህግ ስልጠና ኢንስቲትዩቶች የህግ ባለሙያዎችን የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ብቃት ክህሎት እና ስነምግባር በመመዘን የሙያ ፈቃድ የመስጠት፤

  1. የኢንስቲትዩቱን የምዘናና ብቃት መስፈርቶች እንዲዘጋጁ የማድረግ፤
  2. ፕሮግራም በማዘጋጀት፣ የህግ መምህራንንና የህግ አሰልጣኞችን ምዘናና ብቃት ሂደት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ተግባራዊ በማድረግ የሙያ ብቃታቸዉን የማረጋገጥ፤
  3. የምዘናና ብቃት ማረጋገጥ ስርዓት የመዘርጋት፤

Raeesh

ጥላሁን ደኑ (ዶ/ር)
የህግ ባለሙያዎች ምዘናና ብቃት ማረጋገጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ
ስልክ፡-
የቢሮ፡- +251- 114169636
ሞባይል፡-+251-0917837611
ኢሜል፡-denutilahun8@gmail.com

  1. የስርዓት ዝርጋታዉም በተሳካ መልኩ ከተጠናቀቀ በኋላ የምዘና ሥርዓትን በየተቋማቱ የማስጀመር፡

ከተቋማችን አጋር ጀስቲስ ፎር ኦል ያዘጋጀዉ ሀገር አቀፍ የፍትህ አካላት የጋራ የምክክር መድረክ ላይ

በዚሁም መሰረት የህግ ባለሙያዎች ምዘናና ብቃት ማረጋገጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ የኢንስቲትዩቱን የምዘናና ብቃት መስፈርቶች እንዲዘጋጁ በማድረግ፣ ፕሮግራም በማዘጋጀት፣ የህግ መምህራንንና የህግ አሰልጣኞችን ምዘናና ብቃት ሂደት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ተግባራዊ በማድረግ የሙያ ብቃታቸዉን ለማረጋገጥ የተቋቋመ ክፍል ነዉ፡፡ለዚህም ተግባራዊነት ከ2012 ጀምሮ የምዘናና ብቃት ማረጋገጥ ስርዓት ዝርጋታ ፕሮጀክት እቅድ በመንደፍ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡የስርዓት ዝርጋታዉም በተሳካ መልኩ ከተጠናቀቀ በኋላ ምዘና የሚጀምር ይሆናል፡፡


ለበለጠ መረጃ ያግኙን!
ጥላሁን ደኑ (ዶ/ር) :- የህግ ባለሙያዎች ምዘናና ብቃት ማረጋገጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ
BA,LLB,ARE Degree,LLM,MPA, PhD
ስልክ፡- የቢሮ፡-+251- 114169636
ሞባይል፡-+251-0917837611
ኢሜል፡-denutilahun8@gmail.com


የመረጃ መላኪያ ፖርታል

የተጠቃሚ ስም

የተጠቃሚ ቁልፍ


በ2016 ዓ.ም ስልጠና የሰጠናቸዉ ተቋማት በጥቂቱ


አጋር ተቋማት

የተቋማችን አጋር አዉሮፓን የህብረት
European Union


የተቋማችን አጋር ጀስቲስ ፎር ኦል
Justice for All PF Ethiopia

Our Partner


በ2015 ዓ.ም በጽ/ቤቱ የተዘጋጀ የአረንጓዴ አሻራ

የፌዴራል ፀረ ሙስና ምክትል ኮምሽነር እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት